Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 14:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የኢዮርብዓምም ሚስት እንዲሁ አደረገች፤ ተነሥታም ወደ ሴሎ ሄደች፤ ወደ አኪያም ቤት መጣች። አኪያም ስለ መሸምገሉ ዐይኖቹ ፈዝዘው ነበርና ማየት አልቻለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ያላትን አድርጋ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች። በዚህ ጊዜ አኪያ ከማርጀቱ የተነሣ ዐይኖቹ ፈዝዘው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ይህን ሁሉ አዘጋጅታ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች፤ ነቢዩ አኪያም በዕድሜው ከመሸምገሉ የተነሣ ዐይኖቹ ፈዘው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ይህን ሁሉ አዘጋጅታ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች፤ ነቢዩ አኪያም በዕድሜው ከመሸምገሉ የተነሣ ዐይኖቹ ፈዘው ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እን​ዲሁ አደ​ረ​ገች፤ ተነ​ሥ​ታም እን​ጀራ፥ የወ​ይን ዘለ​ላና አንድ ማሠሮ ማር በመ​ያዝ ወደ ሴሎ ሄደች፤ ወደ አኪ​ያም ቤት ገባች። አኪያ ግን ስለ መሸ​ም​ገሉ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው ነበ​ርና ማየት አል​ቻ​ለም።

参见章节 复制




1 ነገሥት 14:4
12 交叉引用  

ይስሐቅ ሸምግሎ ዓይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፦ ልጄ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆ አለሁ አለው።


የእስራኤልም ዓይኖች ከሸምግልና የተነሣ ከብደው ነበር። ማየትም አይችልም ነበር ወደ እርሱም አቀረባቸው ሳማቸውም አቀፋቸውም።


በዚያን ጊዜም ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ሴሎናዊው ነቢዩ አኪያ በመንገድ ላይ ተገናኘው፤ አኪያም አዲስ ልብስ ለብሶ ነበር፤ ሁለቱም በሜዳው ለብቻቸው ነበሩ።


ኢዮርብዓምም ሚስቱን “ተነሺ፤ የኢዮርብዓምም ሚስት እንደ ሆንሽ እንዳትታወቂ ልብስሽን ለውጪና ወደ ሴሎ ሂጂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እንድነግሥ የነገረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።


ቤት ጠባቆች በሚንቀጠቀጡበት፥ ኃያላን ሰዎችም በሚጎብጡበት፥ ጥቂቶች ሆነዋልና ፈጭታዎች ሥራ በሚፈቱበት፥ በመስኮትም ሆነው የሚመለከቱ በሚጨልሙበት፥ በአደባባይም ደጆቹ በሚዘጉበት ቀን፥


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ዓመት ነበረ፤ ዓይኑ አልፈዘዘም፥ ጉልበቱም አልደነገዘም።


የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፥ በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፥ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።


በዚያም ዘመን እንዲህ ሆነ፥ የዔሊ ዓይኖች ማየት እስኪሳናቸው ድረስ መፍዘዝ ጀምረው ነበር።


ዔሊም የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበረ፥ ዓይኖቹም ማየት እስኪሳናቸው ድረስ ፈዝዘው ነበር።


跟着我们:

广告


广告