Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 12:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችኋል፤ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችኋል፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ፤’ በላቸው፤” ብለው ተናገሩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ ይኸውም አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ!’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ ይኸውም አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ!’ ”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አሁ​ንም አባቴ ከባድ ቀን​በር ጭኖ​ባ​ች​ኋል፥ እኔ ግን በቀ​ን​በ​ራ​ችሁ ላይ እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ች​ኋል፥ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ በላ​ቸው።” ይህም ቃል ሮብ​ዓ​ምን ደስ አሰ​ኘው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 12:11
14 交叉引用  

ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች “‘አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፤ አንተ ግን አቃልልልን፤’ ለሚሉህ ሕዝብ፥ ‘ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች።


ንጉሡም “በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ፤” ብሎ እንደ ተናገረ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ።


እንደ ብላቴኖችም ምክር “አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፤ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ፤” ብሎ ተናገራቸው።


አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በግዞት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አስጨነቀ።


አሁንም ሂዱ፤ ሥሩ፤ ገለባ አይሰጡአችሁም፤ የጡቡን ቁጥር ግን ታመጣላችሁ፤” አላቸው።


ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!


እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለንም? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?


ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚገዛለትን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተወዋለሁ፥ እነርሱም ያርሱአታል ይቀመጡባትማል።


አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ኵርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ አንተም በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራቸው፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ አንተ ቃላቸውን አትፍራ፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።


በዚያም ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሣ ትጮኻላችሁ፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር አልሰማችሁም።


跟着我们:

广告


广告