Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 10:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የማዕዱንም መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም አሠራር፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያሳርገውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ነፍስ አልቀረላትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እንዲሁም በገበታው ላይ የሚቀርበውን መብል፣ የሹማምቱን አቀማመጥ፣ የአስተናባሪዎቹን አቋቋምና የደንብ ልብሳቸውን፣ ጠጅ አሳላፊዎቹን፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያቀረባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዓይነት፥ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፥ የቤተ መንግሥቱን ሠራተኞች የሥራ አደረጃጀት፥ የደንብ ልብሳቸውንም ዓይነት፥ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም የሚያቀርባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀችው በላይ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዐይነት፥ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፥ የቤተ መንግሥቱን ሠራተኞች የሥራ አደረጃጀት፥ የደንብ ልብሳቸውንም ዐይነት፥ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም የሚያቀርባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀችው በላይ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የሰ​ሎ​ሞ​ን​ንም የማ​ዕ​ዱን መብል፥ የብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም አቀ​ማ​መጥ፥ የሎ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ሥር​ዐት፥ አለ​ባ​በ​ሳ​ቸ​ው​ንም፥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹ​ንም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ባየች ጊዜ ተደ​ነ​ቀች።

参见章节 复制




1 ነገሥት 10:5
12 交叉引用  

የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ጥበብ ሁሉ፥ ሠርቶትም የነበረውን ቤት፥


ንጉሡንም አለችው “ስለ ነገርህና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ዝና እውነት ነው።


በእግዚአብሔርም ቤት የዙፋኑን መሠረት ሠራ፤ ስለ አሦርም ንጉሥ በውጭ ያለውን የንጉሡን መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቤት አዞረው።


ለሰፊንና ለሖሳ በምዕራብ በኩል፥ በዐቀበቱም መንገድ ባለው በሸሌኬት በር በኩል በጥበቃ ላይ ጥበቃ ዕጣ ወጣባቸው።


እስከ ዛሬም ድረስ በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረኞች ነበሩ።


እነሆም፥ ንጉሡ በመግቢያው በዓምዱ አጠገብ ሆኖ፥ ከንጉሡም ጋር አለቆችና መለከተኞች ቆመው አየች። የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከቱን ይነፉ ነበር፤ መዘምራንም በዜማ ዕቃ እያዜሙ የምስጋና መዝሙር ይዘምሩ ነበር። ጎቶሊያም ልብስዋን ቀድዳ “ዓመፅ ነው! ዓመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።


የማዕዱንም መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም አሠራር አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም አለባበሳቸውንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያሳርገውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ መንፈስ አልቀረላትም።


አለቃው ግን እርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላ ዘንድ ይቀመጥበታል፥ በበሩ ደጀ ሰላም መንገድ ይገባል በዚያም መንገድ ይወጣል።


አለቃውም በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፥ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ፥ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።


እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ።


እንዲህም ሆነ፥ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በባሕሩም አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነግሥታት ሁሉ፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት የዮርዳኖስን ውኃ እስኪሻገሩት ድረስ እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባቸው ቀለጠ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ነፍስ ከዚያ ወዲያ አልቀረላቸውም።


跟着我们:

广告


广告