Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:44 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካሁኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ሰደደ፤ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 ንጉሡ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ዐብረውት እንዲሄዱ አድርጓል፤ እነርሱም በንጉሡ በቅሎ አስቀመጡት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፥ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ንጉሡም እርሱን ያጅቡት ዘንድ ካህኑን ሳዶቅን፥ ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄን ልጅ በናያንና የቤተ መንግሥቱን ክብር ዘበኞች ልኮአል፤ እነርሱም ንጉሡ በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ እንዲቀመጥ አድርገውታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ነቢ​ዩን ናታ​ንን፥ የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን፥ ከሊ​ታ​ው​ያ​ን​ንና ፈሊ​ታ​ው​ያ​ን​ንም ላከ፤ በን​ጉ​ሡም በቅሎ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:44
10 交叉引用  

አያዓና ይህም ዓና በምድረ በዳ የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ ፍልውኆችን ያገኘ ነው።


አቢሳንም ተከትለው የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያንም ፈሊታው ያንም ኃያላንም ሁሉ ሄዱ፥ የቢክሪንም ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ከኢየሩሳሌም ወጡ።


የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፥ የዳዊትም ልጆች አማካሪዎች ነበሩ።


ንጉሡም አላቸው “የጌታችሁን ባሪያዎች ይዛችሁ ሂዱ፤ ልጄንም ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጡት፤ ወደ ግዮንም አውርዱት፤


ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ብሎ መለሰ “በእውነት ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አነገሠው።


ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት፤ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፤ ከተማይቱም አስተጋባች፤ የሰማችሁትም ድምጽ ይህ ነው።


እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን “እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጦአል፤” አለው።


የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ።


አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤


እኛም በከሊታውያን ደቡብ፥ በይሁዳም ምድር፥ በካሌብም ደቡብ ላይ ዘመትን፥ ጺቅላግንም በእሳት አቃጠልናት አለ።


跟着我们:

广告


广告