Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:42 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፤ አዶንያስም “አንተ መልካም ሰው ነህና፥ መልካም ታወራልናለህና ግባ፤” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ኢዮአብ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ፣ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ደረሰ፤ አዶንያስም፣ “እንደ አንተ ያለ ታማኝ ሰው መልካም ዜና ሳይዝ አይመጣምና ግባ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፥ አዶንያስም፦ “አንተ መልካም ሰው ነህና፥ መልካም ታወራልናለህና ግባ” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 እርሱ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ድንገት ደረሰ፤ አዶንያስም “እስቲ ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለ ሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 እር​ሱም ይህን ሲና​ገር የካ​ህኑ የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን መጣ፤ አዶ​ን​ያ​ስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መል​ካ​ምም ታወ​ራ​ል​ና​ለ​ህና ግባ” አለው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:42
10 交叉引用  

ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፦ እነሆ አንተና ልጅህ አኪማአስ የአብያታርም ልጅ ዮናታን ሁለቱ ልጆቻችሁ በደኅና ወደ ከተማ ተመለሱ።


እነሆ፥ የሳዶቅ ልጅ አኪማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን ልጆቻቸው በዚያ ከእነርሱ ጋር አሉ፥ የምትሰሙትን ሁሉ በእነርሱ እጅ ላኩልኝ።


ዮናታንና አኪማአስ ተገልጠው ወደ ከተማ ይገቡ ዘንድ አልቻሉም ነበርና በዓይንሮጌል ተቀምጠው ነበር፥ አንዲትም ባሪያ ሄዳ ትነግራቸው ነበር፥ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ይነግሩት ነበር።


ዘበኛውም፦ የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማአስ ሩጫ ይመስላል አለ፥ ንጉሡም እርሱ መልካም ሰው ነው፥ መልካም ወሬ ያመጣል አለ።


አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምጽ በሰማ ጊዜ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምጽ ምንድር ነው?” አለ።


ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ብሎ መለሰ “በእውነት ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አነገሠው።


የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን “ክፉ እንጂ መልካም እንደማይናገርልኝ አላልሁህምን?” አለው።


ኢዮራምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ! ሰላም ነውን?” አለ። እርሱም “የእናትህ የኤልዛቤል ግልሙትናዋና መተትዋ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።


ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል አምላኬ።


跟着我们:

广告


广告