Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:40 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ፤ ሕዝቡም ዘፈን ይዘፍኑ ነበር፤ በታላቅም ደስታ ደስ አላቸው፤ ከጩኸታቸውም የተነሣ ምድር ተናወጠች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ሕዝቡ ሁሉ እንቢልታ እየነፋና እጅግ እየተደሰተ አጀበው፤ ከድምፁ የተነሣም ምድሪቱ ተናወጠች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ፥ ሕዝቡም ዘፈን ይዘፍኑ ነበር፥ በታላቅም ደስታ ደስ አላቸው፥ ከጩኸታቸውም የተነሣ ምድር ተናወጠች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ወደ ቤተ መንግሥትም በሚመለሱበት ጊዜ አጅበው ተከተሉት፤ ከድምፃቸው ከፍተኛነት የተነሣ ምድር እስክትናወጥ ድረስ እምቢልታ በመንፋት እየጮኹ ደስታቸውን ገለጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ሕዝ​ቡም ሁሉ እር​ሱን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ከበ​ሮ​ንና መሰ​ን​ቆ​ንም መቱ፥ በታ​ላ​ቅም ደስታ ደስ አላ​ቸው፤ ከጩ​ኸ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች።

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:40
13 交叉引用  

ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ፤ ቀንደ መለከትም ነፉ፤ ሕዝቡም ሁሉ “ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ!” አሉ።


አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምጽ በሰማ ጊዜ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምጽ ምንድር ነው?” አለ።


ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት፤ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፤ ከተማይቱም አስተጋባች፤ የሰማችሁትም ድምጽ ይህ ነው።


እነሆም፥ ንጉሡ እንደ ተለመደው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ፥ ከንጉሡም ጋር አለቆችና መለከተኞች ቆመው አየች፤ የአገሩም ሕዝብ ሁል ደስ ብሎአቸው ቀንደ መለከት ይነፉ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።


የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላቸው፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች። ጎቶልያንም በንጉሡ ቤት አጠገብ በሰይፍ ገደሉአት።


የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፥ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፥ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፥ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ወደ ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው፦


ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፥ በዚያም ሳኦልን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ አነገሡት፥ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ፥ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ።


የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገባ ጊዜ እስራኤል ሁሉ ታላቅ እልልታ አደረጉ፥ ምድሪቱም አስተጋባች።


跟着我们:

广告


广告