Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊትንም አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ ‘አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ!’ ይላሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በዛሬው ቀን ታች ወርዶ ብዙ በሬዎች፣ ኰርማዎችና በጎች ሠውቷል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ የሰራዊቱን አዛዦችና ካህኑን አብያታርንም ጠርቷል። እነሆ፤ አሁን፣ ‘አዶንያስ ለዘላለም ይኑር’ እያሉ ከርሱ ጋራ በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፥ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን። ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፥ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ፦ ‘አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ’ ይላሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 አዶንያስ በዛሬው ዕለት ብዙ ጥጆችንና የሰቡ ኰርማዎችን፥ በጎችን ዐርዶ መሥዋዕት አቅርቦአል፤ ሌሎቹን የንጉሡን ልጆች የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዞአል፤ እነሆ አሁን በዚህ ሰዓት “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ አዶንያስ!” በማለት እየደነፉ ከእርሱ ጋር በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን ጠር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በፊቱ እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፦ አዶ​ን​ያስ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ ይላሉ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:25
19 交叉引用  

የዳዊትም ወዳጅ አርካዊው ኩሲ ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ፦ ሺህ ዓመት ያንግሥህ አለው።


እርሱም ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ ካሁኑንም አብያታርን፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል፤ ባሪያህን ስሎሞንን ግን አልጠራውም።


ናታንም አለ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አንተ ‘ከእኔ በኋላ አዶንያስ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ላይ ይቀመጣል፤’ ብለሃልን?


በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቅቡት፤ ቀንደ መለከትም ነፍታችሁ ‘ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ!’ በሉ።


ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ፤ ቀንደ መለከትም ነፉ፤ ሕዝቡም ሁሉ “ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ!” አሉ።


አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን ፍሪዳዎችንም በዓይንሮጌል አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም ባሪያዎች፥ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ።


እርሱም “መንግሥቱ ለእኔ እንደ ነበረ፥ እስራኤልም ሁሉ ንጉሥ እሆን ዘንድ ፊታቸውን ወደ እኔ አድርገው እንደ ነበረ አንቺ ታውቂያለሽ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኖለታልና መንግሥቱ ከእኔ አልፎ ለወንድሜ ሆኖአል።


የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብተውም ንጉሥ አደረጉትና “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ!” እያሉ እጃቸውን አጨበጨቡ።


እነሆም፥ ንጉሡ እንደ ተለመደው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ፥ ከንጉሡም ጋር አለቆችና መለከተኞች ቆመው አየች፤ የአገሩም ሕዝብ ሁል ደስ ብሎአቸው ቀንደ መለከት ይነፉ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።


ሁሉም ፈጥነው ልባሳቸውን ወሰዱ፤ በሰገነቱ መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት፤ ቀንደ መለከትም እየነፉ፥ “ኢዩ ነግሦአል!” አሉ።


አሁንም እንግዲህ፥ አምላካችን ሆይ! እንገዛልሃለን፥ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን።


በነጋውም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሰዉ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቍርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።


የንጉሡንም ልጅ አውጥተው ዘውዱን ጫኑበት፤ ምስክሩንም ሰጡት፤ አነገሡትም፤ ዮዳሄና ልጆቹም “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ!” እያሉ ቀቡት።


የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።


ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ፦ የታደሙትን፦ እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፥ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፥ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ በሉአቸው አለ።


በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር አሉ።


ሳሙኤልም ለሕዝቡ ሁሉ፦ ከሕዝቡ ሁሉ እርሱን የሚመስል እንደሌለ እግዚአብሔር የመረጠውን ታያላችሁን? አላቸው፥ ሕዝቡም ሁሉ፦ ንጉሥ ሕያው ይሁን እያሉ እልልታ አደረጉ።


跟着我们:

广告


广告