本书并非出自上帝启示,且不属于基督教正典或犹太教塔纳赫的一部分。仅为历史与研究目的而展示。 查看完整说明 መጽሐፈ ጦቢት 9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ሩፋኤል የአደራውን ገንዘብ እንደ ተቀበለ 1 ጦብያም ሩፋኤልን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ 2 “አንተ ወንድሜ አዛርያ ሆይ፥ ሁለት ብላቴኖችንና ግመሎችን ይዘህ የሜዶን ክፍል ወደምትሆን ወደ ራጊስ ወደ ገባኤል ቤት ሂድ፤ የብሩንም መክሊት አምጣ። እርሱንም ወደ ሰርጉ በዓል ጥራው። 3 የሰርጉ በዓል ሳያልቅ እንዳልወጣ ራጉኤል አምሎኛልና። 4 አባቴ ግን ቀኑን ይቈጥራል፤ ብዘገይም ፈጽሞ ያዝናል።” 5 ሩፋኤልም ሄደ፤ በገባኤልም ቤት አደረ፤ ደብዳቤውንም ሰጠው፤ እነዚያንም ከረጢቶች እንደታተሙ አምጥቶ ለሩፋኤል ሰጠው። 6 በጧትም በአንድነት ገሥግሠው ሄዱ፤ ወደ ሰርጉም ደረሱ፤ ጦብያም ያን ብር ባመጣለት ጊዜ ሩፋኤልን መረቀው። |