ማሕልየ መሓልይ 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከአንቺ ጋር እንፈልገው ዘንድ ልጅ ወንድምሽ ወዴት ሄደ? ልጅ ወንድምሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ? 2 ልጅ ወንድሜ በገነቱ መንጋውን ይጠብቅ ዘንድ፥ አበባውንም ይሰበስብ ዘንድ ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ። 3 እኔ የልጅ ወንድሜ ነኝ፥ ልጅ ወንድሜም የእኔ ነው፤ በሱፍ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል። 4 ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥ እንደ ኢየሩሳሌምም ያማርሽ ነሽ፤ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት ታስፈርያለሽ። 5 ዐይኖችሽን ከፊቴ መልሺ፤ እነርሱ አስፈርተውኛልና፤ ጠጕርሽ ከገለዓድ እንደ ታየ እንደ ፍየል መንጋ ነው። 6 ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው። ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ናቸው፥ ቃልሽ ያማረ ነው። 7 ከዝምታሽ በቀር ጕንጮችሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። 8 ስድሳ ንግሥታት፥ ሰማንያም ቁባቶች ቍጥር የሌላቸውም ቈነጃጅት አሉ። 9 ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት፤ ለእናቷ አንዲት ናት፥ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥ ንግሥታትና ቁባቶችም አመሰገኑአት። 10 ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥ እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሓይም የጠራች፥ ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት? 11 ልጅ ወንድሜየወንዙን ዳር ልምላሜ ያይ ዘንድ ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ ይመለከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረደ። 12 በዚያ ጡቶችን እሰጥሃለሁ፥ ሰውነቴም አላወቀችም፥ እንደ አሚናዳብ ሰረገላ አደረገኝ አለች። ብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይ ዘንድ ... ወረድሁ” ይላል። ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ ይመለከት ዘንድ ወደ ገውዝ ገነት ወረደ። 13 በዚያ ጡቶችን እሰጥሃለሁ፥ ሰውነቴም አላወቀችም፥ እንደ አሚናዳብ ሰረገላ አደረገኝ አለች። |