本书并非出自上帝启示,且不属于基督教正典或犹太教塔纳赫的一部分。仅为历史与研究目的而展示。 查看完整说明 መጽሐፈ ዮዲት 3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የሰላም መልእክተኞች 1 እንዲህም ብለው የሰላም መልእክተኞችን ወደ እርሱ ላኩ። 2 “እነሆ፥ እኛ የገናናው ንጉሥ የናቡከደነፆር ባሮች በፊትህ እንኖራለን። በፊትህም እንደ ወደድህ አድርገን። 3 እነሆ፥ ከተሞቻችንና አንባዎቻችንም ሁሉ፥ እርሻችንም ሁሉ፥ መንጋዎቻችንም፥ የመሰማሪያችን ቦታዎች ሁሉ፥ በጎቻችንም በፊትህ ያንተ ናቸው፤ እንደ ወደድህም አድርግ። 4 እነሆ ታላላቆች ከተሞቻችን በእነርሱ የሚኖሩ ሰዎች ባሮችህ ናቸው፤ መጥተህም እንደ ወደድህ አድርግ።” 5 እነዚያም ሰዎች ወደ ሆሎፎርኒስ ደርሰው ይህን ነገር ነገሩት። 6 እርሱም ወደ መንደራቸው ወረደ፤ ሠራዊቱም ከእርሱ ጋር ወረዱ ከፍ ከፍ ያሉ አንባዎችንም አስጠበቀ፥ ከእነርሱም የሚረዱትን የተመረጡ ሰዎችን ወሰደ። 7 ወገኖቻቸው ሁሉና እነርሱም አክሊል ደፍተው እየዘፈኑ፥ በገና እየደረደሩና ከበሮ እየመቱ ተቀበሉት። 8 እርሱ ግን አውራጃቸውን ሁሉ አጠፋ፤ ጣዖቶቻቸውንም ሰበረ፤ አሕዛብም ሁሉ ናቡከደነፆርን ብቻ እንዲያመልኩት፥ ቋንቋዎችና ነገዶች ሁሉ አምላክ እንዲሉት እርሱ የሰውን ሁሉ ጣዖት ያጠፋ ዘንድ ታዝዞ ነበር። 9 በትልቁ በይሁዳ ተራራ አንፃር የገባኢያ ዕጣ ወደሚሆን ወደ ኤስድራሎንም መጣ። 10 በሴቅቶን ከተማና በጌባን ሜዳ መካከልም ሰፈረ፤ ለሠራዊቱም ስንቅ ያዘጋጅ ዘንድ በዚያ አንድ ወር ተቀመጠ። |