ኢዮብ 25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የበልዳዶስ ንግግር 1 አውኬናዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦ 2 “ጥንቱን መፈራት በእርሱ ዘንድ ያለ አይደለምን? በከፍታውም ሁሉን ነገር አድራጊ ነው። 3 ለሌቦች ዕረፍትን የሚሰጥ እንዳለ የሚመስለው አይኑር። የክፋቱስ ወጥመድ የማይመጣበት ማን ነው? 4 ጻድቅ ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ንጹሕ ይሆናል? ከሴትስ የተወለደ ራሱን ንጹሕ ማድረግ እንዴት ይችላል? 5 እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ይሰወራል፤ አያበራምም፤ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሓን አይደሉም። 6 ይልቁንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!” |