Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ኢዮብ 21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የኢ​ዮብ መልስ

1 ኢዮ​ብም መለሰ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦

2 “እኛ አጽ​ና​ና​ነው እን​ዳ​ት​ሉኝ፥ ስሙ፤ ቃሌን ስሙ።

3 እና​ገር ዘንድ ዝም በሉ፤ ከተ​ና​ገ​ርሁ በኋላ ትስ​ቁ​ብ​ኛ​ላ​ች​ሁና፤

4 ሰው የሚ​ዘ​ል​ፈኝ አይ​ደ​ለም፤ ስለ ምንስ አል​ቈ​ጣም?

5 ወደ እኔ ተመ​ል​ከቱ፥ ተደ​ነ​ቁም፤ እጃ​ች​ሁ​ንም በጕ​ን​ጫ​ችሁ ላይ አኑሩ።

6 እኔ ባሰ​ብሁ ቍጥር እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ ጻዕ​ርም ሥጋ​ዬን ይይ​ዛል።

7 ስለ ምን ኀጢ​ኣ​ተ​ኞች በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራሉ? በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ትስ ስለ ምን ያረ​ጃሉ?

8 ዘራ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ጸንቶ ይኖ​ራል፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በዐ​ይ​ና​ቸው ፊት ናቸው።

9 ቤታ​ቸው በብ​ል​ፅ​ግና የተ​ሞላ ነው፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ መቅ​ሠ​ፍት አይ​መ​ጣ​ባ​ቸ​ውም።

10 በሬ​ዎ​ቻ​ቸው አይ​መ​ክ​ኑም፤ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ጨ​ነ​ግ​ፉም፤ በደ​ኅ​ናም ይወ​ል​ዳሉ።

11 እነ​ር​ሱም እንደ በጎች ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠ​በ​ቃሉ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም በፊ​ታ​ቸው ይዘ​ፍ​ናሉ።

12 በገ​ናና መሰ​ንቆ ይዘው ይዘ​ም​ራሉ፤ በመ​ዝ​ሙ​ራ​ቸ​ውም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

13 ዕድ​ሜ​ያ​ቸ​ው​ንም በተ​ድላ ይፈ​ጽ​ማሉ፤ በሲ​ኦል ማረ​ፊ​ያም ይጋ​ደ​ማሉ።

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፦ እን​ዲህ ይሉ​ታል፦ ከእኛ ዘንድ ራቅ፤ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እና​ውቅ ዘንድ አን​ወ​ድ​ድም።

15 እን​ገ​ዛ​ለ​ትስ ዘንድ እርሱ ምን ይች​ላል? ወይስ ወደ እርሱ ብን​ቀ​ርብ ምን ይጠ​ቅ​መ​ናል?

16 “እነሆ፥ በጎ​ነ​ታ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ውስጥ አለች፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንን ሥራ አይ​መ​ለ​ከ​ትም።

17 የኃ​ጥ​ኣን መብ​ራት ትጠ​ፋ​ለች፤ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ትመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለች። የበ​ቀል ቍጣም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤

18 በነ​ፋ​ስም ፊት እንደ ገለባ፥ አውሎ ነፋ​ስም እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ይሆ​ናሉ።

19 ልጆቹ ሀብ​ቱን አያ​ገ​ኙም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብድ​ራ​ቱን ይከ​ፍ​ለ​ዋል። እር​ሱም ያን​ጊዜ ያው​ቃል።

20 ዐይ​ኖቹ ልጆቹ ሲወጉ ያያሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አያ​ድ​ና​ቸ​ውም።

21 የወ​ደ​ደ​ውን በቤቱ ውስጥ ያደ​ር​ጋል። ወራ​ቶ​ቹም ከቍ​ጥር ድን​ገት ይጐ​ድ​ላሉ።

22 ጥን​ቱን ዕው​ቀ​ት​ንና ምክ​ርን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን? በነ​ፍሰ ገዳ​ዩስ የሚ​ፈ​ርድ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?

23 አንድ ሰው በሰ​ላም ተዘ​ልሎ ሲቀ​መጥ፥ በሁ​ሉም ፈጽሞ ደስ ብሎት ሳለ ይሞ​ታል።

24 በው​ስጡ ስብ ሞል​ቶ​አል፥ የአ​ጥ​ን​ቶ​ቹም ቅል​ጥም ፈስ​ሶ​አል።

25 ሌላ​ውም ሰው መል​ካ​ምን ነገር ከቶ ሳይ​በላ በተ​መ​ረ​ረች ነፍሱ ይሞ​ታል።

26 ሁሉም በአ​ፈር ውስጥ በአ​ንድ ላይ ይተ​ኛሉ፤ ትሎ​ችም ይሸ​ፍ​ኗ​ቸ​ዋል።

27 እነሆ፥ ደፍ​ራ​ችሁ፥ በእኔ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት እንደ ተነ​ሣ​ችሁ ዐው​ቄ​አ​ለሁ።

28 እና​ንተ፦ የአ​ለ​ቃው ቤት የት ነው? ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ያደ​ረ​በት ድን​ኳን የት ነው? ብላ​ች​ኋ​ልና።

29 መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎ​ችን ጠይ​ቋ​ቸው፤ ምል​ክ​ታ​ቸ​ው​ንም አታ​ገ​ኙም።

30 ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ክፉ ቀን ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለች፤ በቍጣ ቀንም ይወ​ስ​ዱ​ታል።

31 መን​ገ​ዱን በፊቱ የሚ​ና​ገር ማን ነው? እርሱ የሠ​ራ​ው​ንስ የሚ​መ​ል​ስ​በት ማን ነው?

32 እር​ሱን ግን ወደ መቃ​ብር ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ በመ​ቃ​ብ​ሩም ውስጥ ይጠ​በ​ቃል።

33 የሸ​ለ​ቆው ጓል ይጣ​ፍ​ጥ​ለ​ታል፤ በኋ​ላ​ውም ሰው ሁሉ ይወ​ጣል፤ በፊ​ቱም ቍጥር የሌ​ለው ሰው አለ።

34 ለምን በከ​ንቱ ታጽ​ና​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ? በእ​ና​ንተ ዘንድ ግን ዕረ​ፍት የለ​ኝም።”

跟着我们:



广告