Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ኢዮብ 15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የኤ​ል​ፋዝ ሁለ​ተኛ ንግ​ግር

1 ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦

2 “በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ነፋስ በሆነ ዕው​ቀት ይመ​ል​ሳ​ልን? ሆዱ​ንስ በሥ​ቃይ ይሞ​ላ​ልን?

3 ከከ​ንቱ ነገር፥ ወይስ ከማ​ይ​ጠ​ቅም ንግ​ግር ጋር ይዋ​ቀ​ሳ​ልን?

4 አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ትተ​ሃ​ልን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ፊት እን​ዲህ ያለ​ውን ቃል ትና​ገ​ራ​ለ​ህን?

5 ከአ​ፍህ ንግ​ግር የተ​ነሣ መጠ​ንህ ይታ​ወ​ቃል፥ የኀ​ያ​ላ​ኑ​ንም ቃል አል​ለ​የ​ህም።

6 የሚ​ፈ​ር​ድ​ብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህም ይመ​ሰ​ክ​ሩ​ብ​ሃል።

7 በውኑ ከሰው ቀድ​መህ የተ​ፈ​ጠ​ርህ ሰው አንተ ነህን? ወይስ ከተ​ራ​ሮች በፊት ተፀ​ነ​ስ​ህን?

8 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ትእ​ዛዝ ሰም​ተ​ሃ​ልን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማ​ካ​ሪው አድ​ር​ጎ​ሃ​ልን? ወይስ ጥበ​ብን ለብ​ቻህ አድ​ር​ገ​ሃ​ልን?

9 እኛ የማ​ና​ው​ቀ​ውን አንተ ምን ታው​ቃ​ለህ? እኛስ የማ​ና​ስ​ተ​ው​ለ​ውን አንተ ምን ታስ​ተ​ው​ላ​ለህ?

10 በዕ​ድሜ ከአ​ባ​ትህ የሚ​በ​ልጡ፥ ሽበ​ትም ያላ​ቸው ሽማ​ግ​ሎች ከእኛ ጋር አሉ።

11 ጥቂት ብት​በ​ድል ተገ​ረ​ፍህ፥ ይህም የተ​ና​ገ​ር​ኸው ነገር በዐ​ቅ​ምህ አይ​ደ​ለም።

12 “ልብ​ህስ ለምን ይደ​ፍ​ራል? ዐይ​ኖ​ች​ህስ ለምን ይገ​ላ​ም​ጣሉ?

13 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በቍጣ ትመ​ልስ ዘንድ፤ እን​ደ​ዚ​ህስ ያለ ነገር ከአ​ፍህ ታወጣ ዘንድ፤

14 ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው? ጻድ​ቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተ​ወ​ለደ ማን ነው?

15 እነሆ፥ በቅ​ዱ​ሳኑ እንኳ አይ​ታ​መ​ንም፤ ሰማ​ይም በፊቱ ንጹሕ አይ​ደ​ለም።

16 ይል​ቁ​ንስ አስ​ጸ​ያ​ፊና የረ​ከሰ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እንደ ውኃ የሚ​ጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?

17 “ስማኝ ልን​ገ​ርህ፥ እነ​ሆም ያየ​ሁ​ትን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤

18 ጠቢ​ባን የተ​ና​ገ​ሩ​ትን፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያል​ሰ​ወ​ሩ​ትን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።

19 ምድር ለእ​ነ​ርሱ ብቻ ተሰ​ጥ​ታ​ለ​ችና፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እን​ግዳ ሕዝብ አል​ገ​ባ​ባ​ቸ​ው​ምና።

20 የኃ​ጥእ ሰው ዕድ​ሜው በጭ​ንቅ ያል​ፋል፥ ለግ​ፈኛ የተ​መ​ደቡ ዓመ​ታ​ቱም ሁሉ የተ​ቈ​ጠሩ ናቸው።

21 የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ድም​ፅም በጆ​ሮው ነው፤ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም ይኖር ዘንድ ተስፋ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ጥፋት ይመ​ጣ​በ​ታል።

22 ከጨ​ለማ ተመ​ልሶ እን​ዲ​ወጣ ተስፋ የለ​ውም፥ ለሰ​ይ​ፍም ኀይል ፈጽሞ ተዳ​ር​ጎ​አል።

23 ለአ​ሞ​ራ​ዎ​ችም ምግብ ሆኖ ተሰ​ጥ​ቶ​አል በድን ሆኖ እን​ደ​ሚ​ቈ​ይም እርሱ ራሱ ያው​ቃል። የጨ​ለማ ቀንም እንደ አውሎ ነፋስ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለች።

24 መከ​ራና ጭን​ቀት ይመ​ጡ​በ​ታል፤ በፊት እንደ ተሰ​ለፈ መኰ​ንን ይወ​ድ​ቃል።

25 እጁን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዘር​ግ​ቶ​አ​ልና፥ ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ፊትም አን​ገ​ቱን አደ​ን​ድ​ኖ​አ​ልና።

26 በደ​ን​ዳና አን​ገ​ቱና በወ​ፍ​ራሙ በጋ​ሻው ጕብ​ጕብ፥ ከው​ር​ደት ጋር እየ​ሰ​ገገ ይመ​ጣ​በ​ታ​ልና።

27 በስ​ብም ፊቱን ከድ​ኖ​አ​ልና ስቡ​ንም በወ​ገቡ ላይ አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥

28 በተ​ፈ​ቱም ከተ​ሞች ውስጥ ይኖ​ራል፥ ሰውም በሌ​ለ​ባ​ቸው ቤቶች ይገ​ባል፥ እርሱ ያዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ሌሎች ይወ​ስ​ዱ​ታል።

29 “እርሱ ባለ​ጠጋ አይ​ሆ​ንም፤ ሀብ​ቱም አይ​ጸ​ናም፤ ጥላ​ው​ንም በም​ድር ላይ አይ​ጥ​ልም፤

30 ከጨ​ለማ በም​ንም አያ​መ​ል​ጥም፤ ነፋ​ስም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹን ያደ​ር​ቃ​ቸ​ዋል፥ አበ​ባ​ዎ​ቹም ይረ​ግ​ፋሉ።

31 ለመ​ኖር ተስፋ አያ​ደ​ር​ግም፤ ፍጻ​ሜው ከንቱ ይሆ​ና​ልና።

32 ቀኑ ሳይ​ደ​ርስ መከሩ ይጠ​ፋል፥ ቅር​ን​ጫ​ፉም አይ​ለ​መ​ል​ምም።

33 ጮር​ቃ​ውም ይረ​ግ​ፋል፤ እንደ ወይ​ራም አበባ ይወ​ድ​ቃል።

34 ለኃ​ጥ​ኣን ሁሉ ሞት ምስ​ክ​ራ​ቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀ​ባ​ዮ​ችን ቤት ይበ​ላል።

35 በሆ​ዳ​ቸው ጭን​ቅ​ትን ይፀ​ን​ሳሉ፥ ከንቱ ነገ​ር​ንም ይወ​ል​ዳሉ። ሆዳ​ቸ​ውም ተን​ኰ​ልን ያዘ​ጋ​ጃል።”

跟着我们:



广告