Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ሕዝቅኤል 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


አም​ልኮ ባዕድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤቴ ተቀ​ምጬ ሳለሁ፥ የይ​ሁ​ዳም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በፊቴ ተቀ​ም​ጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላዬ መጣ።

2 እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከወ​ገቡ በታች እንደ እሳት የሚ​መ​ስል የሰው አም​ሳያ ነበረ፤ ከወ​ገ​ቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ አይ​ነት ነበረ።

3 እጅ መሳ​ይ​ንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕ​ሬም ያዘኝ፤ መን​ፈ​ስም በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራእይ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ በር መግ​ቢያ ቅን​አት የተ​ባ​ለው ምስል ወደ አለ​በት አመ​ጣኝ፤

4 እነ​ሆም ቀድሞ በሜዳ እንደ አየ​ሁት ራእይ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር በዚያ ነበረ።

5 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ዐይ​ን​ህን ወደ ሰሜን መን​ገድ አንሣ” አለኝ። ዐይ​ኔ​ንም ወደ ሰሜን መን​ገድ አነ​ሣሁ፤ እነ​ሆም በመ​ሠ​ዊ​ያው በር በሰ​ሜን በኩል በመ​ግ​ቢ​ያው ይህ የቅ​ን​ዓት ምስል ነበረ። ከዚ​ያም ወደ ምሥ​ራቅ ያስ​ገ​ባል።

6 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ከመ​ቅ​ደሴ ያር​ቁኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን፥ ታላ​ቁን ርኵ​ሰት ታያ​ለ​ህን? ደግ​ሞም ተመ​ል​ሰህ ከዚህ የበ​ለጠ ታላቅ ርኵ​ሰት ታያ​ለህ” አለኝ።

7 ወደ አደ​ባ​ባ​ዩም መግ​ቢያ አስ​ገ​ባኝ፤ በአ​የ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ በግ​ንቡ ውስጥ ፉካ ነበረ።

8 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ግን​ቡን ንደ​ለው” አለኝ፤ ግን​ቡ​ንም በነ​ደ​ል​ሁት ጊዜ ደጃፍ አገ​ኘሁ።

9 እር​ሱም፥ “ግባ፤ በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ክፉ​ውን ርኵ​ሰት እይ” አለኝ።

10 እኔም ገባ​ሁና፥ እነሆ በግ​ንቡ ዙሪያ ላይ የተ​ን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች አዕ​ዋ​ፍና እን​ስ​ሳ​ትን ምሳሌ ከን​ቱና ርኩስ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቤት ጣዖ​ታት ሁሉ ተሥ​ለው አየሁ።

11 በፊ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰባ ሰዎ​ችና የሳ​ፋን ልጅ ያእ​ዛ​ንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በእጁ ጥና​ውን ይዞ ነበር፥ የዕ​ጣ​ኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።

12 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በስ​ውር እያ​ን​ዳ​ንዱ በሥ​ዕሉ ቤት የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አይ​ተ​ሃ​ልን? እነ​ርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​የ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን ትቶ​አ​ታል ይላ​ሉና” አለኝ።

13 እር​ሱም፥ “ከዚያ የበ​ለ​ጠ​ውን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ታላቅ ኀጢ​አት ታይ ዘንድ ና” አለኝ።

14 ወደ ሰሜ​ንም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም፥ ሴቶች ለተ​ሙዝ እያ​ለ​ቀሱ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።

15 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አይ​ተ​ሃ​ልን? ደግሞ ከዚህ የበ​ለጠ ርኵ​ሰት ታያ​ለህ” አለኝ።

16 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።

17 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አይ​ተ​ሃ​ልን? በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ይህን ኀጢ​አት ያደ​ርጉ ዘንድ ለይ​ሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድ​ሪ​ቱን በኀ​ጢ​አት ሞል​ተ​ዋ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ዋል፤ እነ​ሆም ቅር​ን​ጫ​ፉን አስ​ረ​ዝ​መ​ዋል። ይዘ​ባ​በ​ታ​ሉም።

18 ስለ​ዚህ እኔ ደግሞ በመ​ዓት እሠ​ራ​ለሁ፤ ዐይኔ አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅ​ርታ አላ​ደ​ር​ግም፤ ወደ ጆሮ​ዬም በታ​ላቅ ድምፅ ቢጮኹ አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም” አለኝ።

跟着我们:



广告