Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ሕዝቅኤል 36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ

1 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ትን​ቢት ተና​ገር፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ በላ​ቸው።

2 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጠላት በእ​ና​ንተ ላይ፦ እሰይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጥፋት፥ ለእኛ ርስት ሆነ​ዋል ብሎ​አ​ልና፤

3 ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉ አሕ​ዛብ አዋ​ር​ደ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤ ውጠ​ዋ​ች​ሁ​ማ​ልና፥ እና​ን​ተም የተ​ና​ጋ​ሪ​ዎች ከን​ፈር መተ​ረ​ቻና የአ​ሕ​ዛብ ማላ​ገጫ ሆና​ች​ኋ​ልና፤

4 ስለ​ዚህ፥ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶች፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎች፥ ለም​ድረ በዳ​ዎች፥ ባዶ ለሆ​ኑ​ትና ለፈ​ረ​ሱት፥ በዙ​ሪያ ላሉት ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ምር​ኮና መሣ​ለ​ቂያ ለሆ​ኑት ከተ​ሞች እን​ዲህ ይላል፦

5 ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤

6 ስለ​ዚህ ስለ እስ​ራ​ኤል ምድር ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችም እን​ዲህ በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ ስለ ተሸ​ከ​ማ​ችሁ በቅ​ን​አ​ቴና በመ​ዓቴ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።

7 ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ በአሉ አሕ​ዛብ ላይ እኔ እጄን አነ​ሣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።

8 “የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! ሕዝቤ ይመጡ ዘንድ ተስፋ ያደ​ር​ጋ​ሉና ወይ​ና​ች​ሁ​ንና ፍሬ​ያ​ች​ሁን ይበ​ላሉ።

9 እነሆ እኔ ለእ​ና​ንተ ነኝና፤ ወደ እና​ን​ተም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ትታ​ረ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ትዘ​ራ​ላ​ች​ሁም፤

10 እኔም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሰዎች ሁሉ ሁሉ​ንም አበ​ዛ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በከ​ተ​ሞ​ችም ሰዎች ይኖ​ሩ​ባ​ቸ​ዋል፤ ባድ​ማ​ዎ​ቹም ስፍ​ራ​ዎች ይሠ​ራሉ።

11 ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም አበ​ዛ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይበ​ዛሉ፤ ያፈ​ሩ​ማል፤ እንደ ጥን​ታ​ች​ሁም ሰዎ​ችን አኖ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቀድ​ሞም እንደ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ችሁ መል​ካም አደ​ር​ግ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

12 ሰዎ​ች​ንም፥ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ና​ንተ ላይ አበ​ዛ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይወ​ር​ሱ​አ​ች​ኋል፤ ርስ​ትም ትሆ​ኑ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ልጅ አልባ አታ​ደ​ር​ጓ​ቸ​ውም።

13 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነ​ርሱ፦ ሰው በላ​ተኛ ነሽ፤ በሕ​ዝ​ብ​ሽም መካ​ከል ልጆ​ች​ሽን አጥ​ፍ​ተ​ሻል ብለ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤

14 ስለ​ዚህ ዳግ​መኛ ሰው በላ​ተኛ አት​ሆ​ኝም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን ልጅ አልባ አታ​ደ​ር​ጊም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

15 ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ አላ​ሰ​ማ​ብ​ሽም፤ ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ውር​ደት አት​ሸ​ከ​ሚም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን አታ​ሰ​ና​ክ​ዪም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


የእ​ስ​ራ​ኤል አዲስ ሕይ​ወት

16 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦

17 “የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በም​ድ​ራ​ቸው በተ​ቀ​መጡ ጊዜ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በጣ​ዖ​ታ​ቸው አረ​ከ​ሱ​አት፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በፊቴ እንደ አደፍ ርኵ​ሰት ነበረ።

18 በም​ድር ላይ ስለ አፈ​ሰ​ሱት ደም፥ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስለ አረ​ከ​ሱ​አት መዓ​ቴን አፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤

19 ወደ አሕ​ዛ​ብም በተ​ን​ኋ​ቸው፤ ወደ ሀገ​ሮ​ችም ዘራ​ኋ​ቸው፤ እንደ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውና እንደ በደ​ላ​ቸ​ውም መጠን ፈረ​ድ​ሁ​ባ​ቸው።

20 ወደ ገቡ​ባ​ቸ​ውም ወደ አሕ​ዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነ​ር​ሱን፦ ከም​ድ​ራ​ቸው የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ እነ​ዚህ ናቸው ሲሉ​አ​ቸው ቅዱስ ስሜን አረ​ከሱ።

21 እኔ ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በመ​ጡ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ስለ አረ​ከ​ሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራ​ሁ​ላ​ቸው።

22 “ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በገ​ባ​ች​ሁ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ስላ​ረ​ከ​ሳ​ች​ሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እና​ንተ የም​ሠራ አይ​ደ​ለ​ሁም።

23 በአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ የረ​ከ​ሰ​ውን፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያረ​ከ​ሳ​ች​ሁ​ትን ገናና ስሜን እቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ና​ቸ​ውም ዘንድ በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ አሕ​ዛብ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

24 ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ገዛ ምድ​ራ​ች​ሁም እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።

25 ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።

26 አዲስ ልብ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ የድ​ን​ጋ​ዩ​ንም ልብ ከሥ​ጋ​ችሁ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።

27 መን​ፈ​ሴ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ በት​እ​ዛ​ዜም እን​ድ​ት​ሄዱ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ዴ​ንም ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ ታደ​ር​ጉ​ት​ማ​ላ​ችሁ።

28 ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋት ምድር ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ብም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ።

29 ከር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እህ​ል​ንም እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ው​ማ​ለሁ፤ ራብ​ንም አላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።

30 ደግ​ሞም የራ​ብን ስድብ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እን​ዳ​ት​ሸ​ከሙ የዛ​ፍን ፍሬና የእ​ር​ሻ​ውን መከር አበ​ዛ​ለሁ።

31 ክፉ​ውን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና መል​ካም ያይ​ደ​ለ​ውን ሥራ​ች​ሁ​ንም ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁና ስለ ርኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ራሳ​ች​ሁን ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ።

32 ይህን የሠ​ራሁ ስለ እና​ንተ እን​ዳ​ይ​ደለ በእ​ና​ንተ ዘንድ የታ​ወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ መን​ገ​ዳ​ችሁ እፈ​ሩና ተዋ​ረዱ።

33 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ በአ​ነ​ጻ​ኋ​ችሁ ጊዜ በከ​ተ​ሞች ሰዎ​ችን አኖ​ራ​ለሁ፤ ባድ​ማ​ዎ​ቹም ስፍ​ራ​ዎች ይሠ​ራሉ።

34 ባድማ የነ​በ​ረች፥ በመ​ን​ገ​ደ​ኛም ሁሉ ዐይን ዘንድ ባድማ የነ​በ​ረች ምድር ትታ​ረ​ሳ​ለች።

35 ሰዎ​ችም ባድማ የነ​በ​ረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆና​ለች፤ የፈ​ረ​ሱት፥ ባድማ የሆ​ኑት፥ የጠ​ፉ​ትም ከተ​ሞች ተመ​ሽ​ገ​ዋል፤ ሰውም የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ሆነ​ዋል ይላሉ።

36 በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም የቀ​ሩት አሕ​ዛብ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ረ​ሱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች እንደ ሠራሁ፥ ውድማ የሆ​ነ​ው​ንም እንደ ተከ​ልሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፥ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።

37 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ​ዚህ ደግሞ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይሹ​ኛል፤ ሰው​ንም እንደ መንጋ አበ​ዛ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።

38 እንደ ተቀ​ደሱ በጎች፥ በበ​ዓ​ላ​ቶ​ችዋ ቀን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በጎች እን​ዲሁ የፈ​ረ​ሱት ከተ​ሞች በሰ​ዎች መንጋ ይሞ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”

跟着我们:



广告