Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ሕዝቅኤል 35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት

1 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦

2 “የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን ወደ ሴይር ተራራ መልስ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​በት፤

3 እን​ዲ​ህም በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ፤ እጄን እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ባድ​ማና ውድ​ማም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።

4 ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም አፈ​ራ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ባድማ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።

5 የዘ​ለ​ዓ​ለም ጠላት ሁነ​ሃ​ልና፥ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ በኀ​ይ​ለ​ኛ​ይቱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በሰ​ይፍ እጅ ጥለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና፤

6 ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! በደም እንደ በደ​ልህ ደም ያሳ​ድ​ድ​ሃል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

7 የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ውድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም አጠ​ፋ​ለሁ።

8 ተራ​ሮ​ች​ህ​ንም በተ​ገ​ደ​ሉት ሰዎች እሞ​ላ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ች​ህና በሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችህ፥ በፈ​ሳ​ሾ​ች​ህም ሁሉ ላይ በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደ​ሉት ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ።

9 ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ህም ሰው የማ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።

10 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፥ እነ​ዚህ ሁለቱ ሕዝ​ቦች፥ እነ​ዚ​ህም ሁለቱ ሀገ​ሮች ለእኔ ይሆ​ናሉ፤ እኔም እወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤

11 ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝ! እንደ ቍጣህ መጠን፥ እነ​ር​ሱ​ንም ጠል​ተህ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኸው እንደ ቅን​አ​ትህ መጠን እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በፈ​ረ​ድ​ሁ​ብ​ህም ጊዜ በእ​ነ​ርሱ ዘንድ የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ።

12 አን​ተም፦ ፈር​ሰ​ዋል፤ መብ​ልም ሆነው ለእኛ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል ብለህ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ስድብ ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰማ​ሁት ታው​ቃ​ለህ።

13 አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”

14 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፥ “ምድር ሁሉ ደስ ሲላት አን​ተን ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።

15 የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እን​ዳ​ለህ፥ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! አን​ተና መላው ኤዶ​ም​ያስ ባድማ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”

跟着我们:



广告