1 ዜና መዋዕል 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የብንያም ትውልድ 1 ብንያምም በኵሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥ ሦስተኛውንም አሐራን፤ 2 አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ። 3 ለቤላም ልጆች ነበሩት፤ አዳር፥ ጌራ፥ አቤሁድ፤ 4 አቤሱ፥ ናዕማን፥ አሖዋ፤ 5 ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም። 6 እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ ወደ መነሐትም ተማረኩ፤ 7 ናዕማን፥ አኪያ፥ ጌራ፥ እነርሱም ተማረኩ። ዖዛንና አሂሑድን ወለደ። 8 ሰሐራይምም ሚስቶቹን ሑሴምንና በዕራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆችን ወለደ። 9 ከሚስቱ ከሖዲሽ ዮባብን፥ ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፤ 10 ኢያሱብን፥ ሻክያን፥ ሜርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ። 11 ከሑሲምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ። 12 የኤልፍዓልም ልጆች ዖቤድ፥ ሚሳም፥ ኦኖንና ሎድን፥ መንደሮቻቸውንም የሠራ ሳሜር፤ 13 በሪዓ፥ ሰማዕ ነበሩ፤ እነርሱም የጌትን ነዋሪዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ 14 ወንድሞቹም ሶሲቅና ይሬሞት፤ 15 ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔዴር፤ 16 ሚካኤል፥ የሴፋ፥ ዮሐ፥ የበሪዓም ልጆች፤ 17 ዝባድያ፥ ሜሱላም፥ ሕዝቂ፥ ሔቤር፤ 18 ይሰምራይ፥ ይዝሊያ፥ ዮባብ፥ 19 የኤልፍዓል ልጆች ያቂም፥ ዝክሪ፥ ዘብዲ፥ 20 ኤሊዔናይ፥ ጼልታይ፥ ኤሊኤል፤ 21 ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሲምራት፥ የሰሜኤ ልጆች፤ 22 ይሰጳን፥ ዖቤድ፥ ኤሊኤል፤ 23 ዓብዶን፥ ዝክሪ፥ ሐናን፤ 24 ሐናንያ፥ አንበሪ፥ ኤላም፤ አናቶትያ፥ 25 ይቲን፥ ይፍዴያ፥ ፋኑኤል፥ የሶሴቅ ልጆች፤ 26 ሸምሸራይ፥ ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፤ 27 ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች። 28 እነዚህ በትውልዶቻቸው አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። 29 የገባዖን አባት በገባዖን ይኖር ነበር የሚስቱም ስም መዓካ ነበር፤ 30 የበኵር ልጁ ዓብዶን፥ ሱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ኔር፥ ናዳብ፥ 31 ጌዶርና፥ ወንድሙ ዛኪር ሜቅሎት፤ 32 ሜቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ተቀመጡ። የንጉሥ ሳኦል ትውልድ 33 ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስበኣልን ወለደ። 34 የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ። 35 የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ። 36 አካዝም ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ማሴዕን ወለደ። 37 ማሴዕም በዓናን ወለደ፤ ልጁም ራፋያ ነበረ፤ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤ 38 ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ በኬርዩ፥ እስማኤል፥ ሰዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ ሁሉ የአሴል ልጆች ነበሩ። 39 የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኤያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት። 40 የኡላም ልጆች ጽኑዓን ኀያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ አምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ። |