1 ዜና መዋዕል 25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የቤተ መቅደስ መዘምራን 1 ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶትምም ልጆች በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም የሚዘምሩ ሰዎችን ለማገልገል ለዩ፤ በየአገልግሎታቸውም ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ። 2 ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ናታንያ፥ ኤራኤል፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች የንጉሡ ቀራቢዎች ነበሩ። 3 ከኤዶትም የኤዶትም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ሱሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መታትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ከአባታቸው ከኤዶትም ጋር በበገና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር። 4 ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤል፥ ኢየሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጌዶላቲ፥ ሮማንቴዔዜር፥ ዮስብቃሳ፥ ሜኤላቴ፥ ሆቴር፥ መሐዝዮት፤ 5 እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ ያደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል በንጉሡ ፊት የሚዘምረው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው። 6 እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና፥ በመሰንቆም ከአባታቸው ጋራ የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል ወደ ንጉሡ ቀርበው ያመሰግኑ ነበር። አሳፍም ኤዶትምም ኤማንም ያመሰግኑ ነበር። 7 የብልሃተኞቹም ቍጥር እግዚአብሔርን ለማመስገን ከሚያውቁ ከወንድሞቻቸው ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ። 8 ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹም ታላቁም፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ እነርሱም ፍጹማንና የተማሩ ነበሩ። 9 የመጀመሪያው ዕጣ ለአሳፍ ወገን ለዮሴፍ ለወንድሞቹና ለልጆቹ ለዐሥራ ሁለቱ ደረሳቸው፤ ሁለተኛውም ዕጣ ለጎዶልያስ ለልጆቹና ለወንድሞቹ ለዐሥራ ሁለቱ ደረሳቸው፤ 10 ሦስተኛው ለዘኩር ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 11 አራተኛው ለይጽሪ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 12 አምስተኛው ለናታንያስ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ። 13 ስድስተኛው ለቡቅያ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 14 ሰባተኛው ለይስርኤል ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 15 ስምንተኛው ለኢያስያ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 16 ዘጠነኛው ለማታንያስ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 17 ዐሥረኛው ለሰሜኢ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 18 ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 19 ዐሥራ ሁለተኛው ለኢሰብያ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 20 ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 21 ዐሥራ አራተኛው ለማታትያስ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 22 ዐሥራ አምስተኛው ለኢየሪሙት ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 23 ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 24 ዐሥራ ሰባተኛው ለዮስባቃጥ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 25 ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 26 ዐሥራ ዘጠነኛው ለማኤላቲ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 27 ሃያኛው ለኤልያታ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 28 ሃያ አንደኛው ለኦትሪ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 29 ሃያ ሁለተኛው ለጌዶላቲ ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 30 ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት ለልጆቹም፥ ለወንድሞቹም፥ ለዐሥራ ሁለቱ፤ 31 ሃያ አራተኛው ለሮማንቴዔዜር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለዐሥራ ሁለቱ ወጣ። |