1 ዜና መዋዕል 24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የካህናት አገልግሎት ድርሻ 1 የአሮንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ። 2 ናዳብና አብዩድ ግን ልጆች ሳይወልዱ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ የአሮን ልጆች አልዓዛርና ኢታምርም ካህናት ሆነው አገለገሉ። 3 ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ሳዶቅን፥ ከኢታምርም ልጆች አቤሜሌክን እንደ ቍጥራቸው፥ እንደ አገልግሎታቸውና እንደ እየአባቶቻቸው ቤቶች ከፍሎ መደባቸው። 4 የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምር ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ዐሥራ ስድስት አለቆች፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ። 5 ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የንዋያተ ቅዱሳቱና የእግዚአብሔር ቤት አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ። 6 ከሌዋውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሳምያስ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት ፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቤሜሌክ ፊት ፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ። 7 መጀመሪያውም ዕጣ ለኢያሬብ ወጣ፤ ሁለተኛውም ለኢያድያ፥ 8 ሦስተኛውም ለካሬም፥ አራተኛውም ለሴዓሪን፥ 9 አምስተኛውም ለመልክያ፥ ስድስተኛውም ለሜዒያኢም፥ 10 ሰባተኛውም ለአቆስ፥ ስምንተኛው ለአብያ፥ 11 ዘጠነኛው ለኢያሱ፥ ዐሥረኛው ለሴኬንያ፥ 12 ዐሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፥ ዐሥራ ሁለተኛው ለኤልያቄም፥ 13 ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፋዕ፥ ዐሥራ አራተኛው ለኤሳባእ፥ 14 ዐሥራ አምስተኛው ለቤልጋዕ፥ ዐሥራ ስድስተኛው ለኤሜር፥ 15 ዐሥራ ሰባተኛው ለኢያዜር፥ ዐሥራ ስምንተኛው ለአፌስ፥ 16 ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታሕያ፥ ሃያኛው ለሕዝቄል፥ 17 ሃያ አንደኛው ለአኬኖ፥ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙሄል፥ 18 ሃያ ሦስተኛው ለደላኢያ፥ ሃያ አራተኛው ለሙዓዚ። 19 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ በአባታቸው በአሮን እጅ እንደ ተሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት ይገቡ ዘንድ እንደ እየአገልግሎታቸው ቍጥራቸው ይህ ነበረ። የሌዋውያን የስም ዝርዝር 20 ከቀሩትም የሌዊ ልጆች፤ ከእንበረም ልጆች ስባሄል፤ ከስባሄል ልጆች ኢያዳእያ፤ 21 ከአረብያም ልጆች የአረብያ ልጅ አራድያ፥ አለቃው ኢያስያስ፤ 22 ከኢስዓራውያን ሰሎሞት፤ ከሰሎሞት ልጆች ኤናት፤ 23 ከኢዩዲዩ ልጆች አለቃው ይሪያ፥ ሁለተኛው አማርያ፥ ሦስተኛው ኢያዚሄል፥ አራተኛው ኢያቁምያ፤ 24 የኢያዝሄል ልጅ ሚካ፤ የሚካ ልጅ ሳሜር፤ 25 የሚካ ወንድም ኢሳእያ፤ የኢሳእያ ልጅ ዘካርያስ፤ 26 የሜራሪ ልጆች ሞዓሊና ሐሙሲ፤ የዖዝያስ ልጅ ባኒ፤ 27 የሜራሪ ልጆች፤ ከዖዝያ ይሰዓም፥ ዝኩር፥ አብዲ፤ 28 የሞዓሊ ልጅ አልዓዛር፥ እርሱም ልጆች አልነበሩትም፤ 29 ከቂስ፤ የቂስ ልጅ አራሜሄል፤ 30 የሐሙሲ ልጆች፤ ሞዓሊ፥ ኤዳር፥ ኢያሪሞት። እነዚህ እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ። 31 እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቤሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላላቆች እንደ ታናናሽ ወንድሞቻቸው፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ። |