መዝሙር 67 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 67 ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር፤ ማሕሌት። 1 እግዚአብሔር ይማረን፤ ይባርከን፤ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ ሴላ 2 መንገድህ በምድር ላይ፣ ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ። 3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ። 4 ለሕዝቦች በቅን ስለምትፈርድላቸው፣ ሰዎችንም በምድር ላይ ስለምትመራ፣ ሕዝቦች ደስ ይበላቸው፤ በእልልታም ይዘምሩ። ሴላ 5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ። 6 ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤ እግዚአብሔር፣ አምላካችን ይባርከናል። 7 እግዚአብሔር ይባርከናል፤ የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ እርሱን ይፈሩታል። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.