መዝሙር 149 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 149 1 ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ። 2 እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ። 3 ስሙን በሽብሸባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት። 4 እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤ የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል። 5 ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤ በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ። 6 የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣ ባለሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤ 7 በዚህ ሕዝቦችን ይበቀላሉ፤ ሰዎችንም ይቀጣሉ፤ 8 ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣ መኳንንታቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፤ 9 ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው። ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.