Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

መዝሙር 137 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


መዝሙር 137

1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።

2 እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣ በገናዎቻችንን ሰቀልን።

3 የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤ የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።

4 የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!

5 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣ ቀኝ እጄ ትክዳኝ።

6 ሳላስታውስሽ ብቀር፣ ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣ ምላሴ ከትናጋዬ ጋራ ትጣበቅ።

7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣ ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤ ደግሞም፣ “አፍርሷት፤ ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።

8 አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤ በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሽው ድርጊት፣ የእጅሽን የሚሰጥሽ ብፁዕ ነው፤

9 ብፁዕ ነው፤ ሕፃናትሽንም ይዞ፣ በዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告