1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ ሐሳቤ ለዐጕል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም።
2 ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሠኘኋት፤ ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።
3 እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.