መዝሙር 129 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 129 መዝሙረ መዓርግ። 1 እስራኤል እንዲህ ይበል፦ “ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ 2 በርግጥ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ ዳሩ ግን ድል አላደረጉኝም። 3 ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ ትልማቸውንም አስረዘሙት።” 4 እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው፤ የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለው። 5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። 6 ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤ 7 ደግሞም ለዐጫጅ እጁን፣ ለነዶ ሰብሳቢ ዕቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ። 8 መንገድ ዐላፊዎችም፣ “የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.