Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

መዝሙር 124 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


መዝሙር 124
የዳዊት መዝሙረ መዓርግ።

1 እስራኤል እንዲህ ይበል፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ባይሆን ኖሮ፣

2 ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ባይሆን ኖሮ፣

3 ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፣ በቁመናችን በዋጡን ነበር፤

4 ጐርፍ ባጥለቀለቀን፣ ፈረሰኛው ውሃ ባሰጠመን፣

5 ደራሽ ውሃም ጠራርጎ በወሰደን ነበር።

6 በጥርሳቸው ከመዘንጠል የጠበቀን፣ እግዚአብሔር ይባረክ።

7 ነፍሳችን እንደ ወፍ፣ ከዐዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም አመለጥን።

8 የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ የእግዚአብሔር ስም ረዳታችን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告