መዝሙር 122 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 122 የዳዊት መዝሙረ መዓርግ። 1 “ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ” ባሉኝ ጊዜ፣ ደስ አለኝ። 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግሮቻችን ከደጅሽ ውስጥ ቆመዋል። 3 ኢየሩሳሌም እጅግ እንደ ተጠጋጋች፣ ከተማ ሆና ተሠርታለች። 4 ለእስራኤል በተሰጠው ሥርዐት መሠረት፣ የእግዚአብሔርን ስም ለማመስገን፣ የእግዚአብሔር ነገዶች ወደዚያ ይመጣሉ። 5 በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የሆኑት፣ የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል። 6 እንዲህ ብላችሁ ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፤ “የሚወድዱሽ ይለምልሙ፤ 7 በቅጥርሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤ በምሽግሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን”። 8 ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ፣ “በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ። 9 ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት፣ በጎነትሽን እሻለሁ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.