መዝሙር 121 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 121 መዝሙረ መዓርግ። 1 ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል? 2 ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል። 3 እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም። 4 እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም። 5 እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል። 6 ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤ ጨረቃም በሌሊት ጕዳት አታመጣብህም። 7 እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ ነፍስህንም ይንከባከባታል። 8 እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.