መዝሙር 120 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 120 መዝሙረ መዓርግ። 1 በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ። 2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ ከአታላይ ምላስም አድነኝ። 3 ሐሰተኛ አንደበት ሆይ፤ ምን ይከፈልህ? ከዚህስ የባሰ ምን ይደረግብህ? 4 በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣ በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል። 5 በሜሼኽ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ! 6 ሰላምን በሚጠሉ መካከል፣ ነፍሴ እጅግ ብዙ ጊዜ ኖረች። 7 እኔ የሰላም ሰው ነኝ፤ እነርሱ ግን በተናገርሁ ጊዜ ጦርነትን ይሻሉ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.