መዝሙር 114 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 114 1 እስራኤል ከግብጽ ወጥቶ ሲሄድ፣ የያዕቆብም ቤት ቋንቋው ልዩ ከሆነ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ፣ 2 ይሁዳ የእግዚአብሔር መቅደስ፣ እስራኤልም ግዛቱ ሆነ። 3 ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ። 4 ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ። 5 አንቺ ባሕር፤ የሸሸሽው አንቺም ዮርዳኖስ ያፈገፈግሽው ለምንድን ነው? 6 እናንተ ተራሮች እንደ አውራ በግ፣ ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ለምን ዘለላችሁ? 7 ምድር ሆይ፤ በጌታ ፊት፣ በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፤ 8 እርሱ ዐለቱን ወደ ኵሬ፣ ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.