Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ነህምያ 7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ።

2 በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው።

3 ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያድርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።


ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር

4 ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር።

5 ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱንና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።

6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ።

7 የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከዓዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከሚስጴሬት፣ ከበጉዋይ፣ ከነሑምና ከበዓና ጋራ ነው። የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር፦

8 የፋሮስ ዘሮች 2,172

9 የሰፋጥያስ ዘሮች 372

10 የኤራ ዘሮች 652

11 የኢያሱና የኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,818

12 የኤላም ዘሮች 1,254

13 የዛቱዕ ዘሮች 845

14 የዘካይ ዘሮች 760

15 የቢንዊ ዘሮች 648

16 የቤባይ ዘሮች 628

17 የዓዝጋድ ዘሮች 2,322

18 የአዶኒቃም ዘሮች 667

19 የበጉዋይ ዘሮች 2,067

20 የዓዲን ዘሮች 655

21 በሕዝቅያስ የትውልድ ሐረግ የአጤር ዘሮች 98

22 የሐሱም ዘሮች 328

23 የቤሳይ ዘሮች 324

24 የሐሪፍ ዘሮች 112

25 የገባዖን ዘሮች 95

26 የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች 188

27 የዓናቶት ሰዎች 128

28 የቤት አዝሞት ሰዎች 42

29 የቂርያትይዓይሪም፣ የከፊራና የብኤሮት ሰዎች 743

30 የራማና የጌባዕ ሰዎች 621

31 የማክማስ ሰዎች 122

32 የቤቴልና የጋይ ሰዎች 123

33 የሌላው ናባው ሰዎች 52

34 የሌላው ኤላም ዘሮች 1,254

35 የካሪም ዘሮች 320

36 የኢያሪኮ ዘሮች 345

37 የሎድ፣ የሐዲድና የኦኖም ዘሮች 721

38 የሴናዓ ዘሮች 3,930

39 ካህናቱ፦ ከኢያሱ ቤተ ሰብ የዮዳኤ ዘሮች 973

40 የኢሜር ዘሮች 1,052

41 የፋስኮር ዘሮች 1,247

42 የካሪም ዘሮች 1,017

43 ሌዋውያኑ፦ በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች 74

44 መዘምራኑ፦ የአሳፍ ዘሮች 148

45 በር ጠባቂዎቹ፦ የሰሎም፣ የአጤር፣ የጤልሞን፣ የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች 138

46 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ የሲሐ፣ የሐሡፋ፣ የጠብዖት ዘሮች፣

47 የኬራስ፣ የሲዓ፣ የፋዶን፣

48 የልባና፣ የአጋባ፣ የሰምላይ ዘሮች፣

49 የሐናን፣ የጌዴል፣ የጋሐር ዘሮች፣

50 የራያ፣ የረአሶን፣ የኔቆዳ ዘሮች፣

51 የጋሴም፣ የዖዛ፣ የፋሴሐ ዘሮች፣

52 የቤሳይ፣ የምዑኒም፣ የንፉሰሲም ዘሮች፣

53 የበቅቡቅ፣ የሐቁፋ፣ የሐርሑር ዘሮች፣

54 የበስሎት፣ የምሒዳ፣ የሐርሳ ዘሮች፣

55 የበርቆስ፣ የሲሣራ፣ የቴማ ዘሮች፣

56 የንስያና፣ የሐጢፋ ዘሮች።

57 የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፣

58 የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፣

59 የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈክራት ሐፂቦይምና የአሞን ዘሮች።

60 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392

61 ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የመጡ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦

62 የዳላያ፣ የጦብያና፣ የኔቆዳ ዘሮች 642

63 ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል።

64 እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ።

65 ስለዚህ አገረ ገዥውም ኡሪምና ቱሚም የሚይዝ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው።

66 የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤

67 ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 245 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው።

68 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣ 435 ግመሎችና

69 6,720 አህዮችም ነበሯቸው።

70 አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዥውም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።

71 ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 ምናን ብር ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።

72 የቀረው ሕዝብ በአጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 ምናን ብርና 67 ልብሰ ተክህኖ ነበር።

73 ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ። ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告