Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ናሆም 3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


ለነነዌ

1 ለደም ከተማ ወዮላት! ሐሰት፣ ዘረፋም ሞልቶባታል፤ ብዝበዛዋ ተግዞ አያልቅም።

2 የጅራፍ ድምፅ፣ የመንኰራኵር ኳኳቴ፣ የፈጣን ፈረስ ኰቴ፣ የሠረገሎች ድምፅ ተሰምቷል።

3 ፈረሰኛው ይጋልባል፤ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፤ ጦር ያብረቀርቃል። የሞተው ብዙ ነው፤ ሬሳ በሬሳ ሆኗል፤ ስፍር ቍጥር የለውም፤ መተላለፊያ አልተገኘም።

4 ይህ ሁሉ የሆነው ቅጥ ባጣች፣ አሳሳችና መተተኛ በሆነች ዘማዊት ምክንያት ነው፤ ይህች የጠንቋዮች እመቤት በዝሙቷ አሕዛብን፣ በጥንቈላዋም ሕዝቦችን ባሪያ ያደረገች ናት።

5 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ፤ ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልበዋለሁ፤ ዕርቃንሽን ለአሕዛብ፣ ኀፍረትሽንም ለነገሥታት አሳያለሁ።

6 ቈሻሻ እደፋብሻለሁ፤ እንቅሻለሁ፤ ማላገጫም አደርግሻለሁ።

7 የሚያዩሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሹ፣ ‘ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል?’ ይላሉ፤ የሚያጽናናሽንስ ከወዴት አገኛለሁ?”

8 አንቺ በአባይ ወንዝ አጠገብ ካለችው፣ በውሃ ከተከበበችው፣ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን? ወንዙ መከላከያዋ፣ ውሃውም ቅጥሯ ነው።

9 ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ።

10 ይሁን እንጂ በምርኮ ተወሰደች፤ ተሰድዳም ሄደች። በየመንገዱ ማእዘን ላይ፣ ሕፃናቷ ተፈጠፈጡ፤ በመሳፍንቷ ላይ ዕጣ ተጣለ፤ ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።

11 አንቺ ደግሞ ትሰክሪአለሽ፤ ትደበቂአለሽ፣ ከጠላትም መሸሸጊያ ትፈልጊአለሽ።

12 ምሽጎችሽ ሁሉ ሊበሉ እንደ ደረሱ የበኵራት በለስ ፍሬ ናቸው፤ በሚወዛወዙበት ጊዜ፣ ፍሬዎቹ በበላተኛው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።

13 እነሆ፤ ጭፍሮችሽ፣ ሁሉም ሴቶች ናቸው! የምድርሽ በሮች፣ ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤ መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቷቸዋል።

14 ለከበባው ውሃ ቅጅ፤ መከላከያሽን አጠናክሪ፤ የሸክላውን ዐፈር ፈልጊ፤ ጭቃውን ርገጪ፤ ጡቡንም ሥሪ።

15 በዚያ እሳት ይበላሻል፤ ሰይፍ ይቈርጥሻል፤ እንደ ኵብኵባም ይግጥሻል። እንደ ኵብኵባ ርቢ፤ እንደ አንበጣም ተባዢ።

16 ከሰማይ ከዋክብት እስኪበልጡ ድረስ፣ የነጋዴዎችሽን ቍጥር አበዛሽ፤ ምድሪቱን ግን እንደ አንበጣ ግጠው አሟጠጡ፤ ከዚያ በርረው ሄዱ።

17 ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣ መኳንንትሽም በብርድ ቀን በቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ ኵብኵባ ናቸው፤ ፀሓይ ሲወጣ ግን ይበርራሉ፤ ወዴት እንደሚበርሩም አይታወቅም።

18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፤ እረኞችህ አንቀላፉ፤ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፤ ሕዝብህ ሰብሳቢ ዐጥተው፣ በተራራ ላይ ተበትነዋል።

19 ቍስልህን ሊፈውስ የሚችል የለም፤ ስብራትህም ለሞት የሚያደርስ ነው። ስለ አንተ የሰማ ሁሉ፣ በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፤ ወሰን የሌለው ጭካኔህ ያልነካው ማን አለና?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告