Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ዘሌዋውያን 3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


የኅብረት መሥዋዕት

1 “ ‘ማንኛውም ሰው የሚያቀርበው ቍርባን ከላሞች መንጋ የሚቀርብ የኅብረት መሥዋዕት ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስት በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።

2 በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይረደው፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።

3 ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያምጣ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ በሆድ ዕቃው ላይ ያለውን ሥብ ሁሉ፣

4 ሁለቱን ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም የጕበቱን መሸፈኛ፣ ከኵላሊቶቹ ጋራ አንድ ላይ አውጥቶ ያቅርብ።

5 የአሮንም ልጆች በመሠዊያው በሚነድደው ዕንጨት ላይ ባለው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አድርገው ያቃጥሉት፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ይሆናል።

6 “ ‘ከበግ ወይም ከፍየሉ መንጋ ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርብ ከሆነ፣ እንከን የሌለበትን ተባዕት ወይም እንስት ያቅርብ።

7 መሥዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነም፣ በእግዚአብሔር ፊት ያምጣው፤

8 በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።

9 ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ እንከን የሌለው መሥዋዕት ያምጣ፤ ሥቡን፣ እስከ ጀርባ ዐጥንቱ ድረስ የተቈረጠ ላቱን በሙሉ፣ የሆድ ዕቃውን የሸፈነውን ሥብ፣ ከሆድ ዕቃው ጋራ የተያያዘውን ሥብ ሁሉ፣

10 ሁለቱን ኵላሊቶች፣ ኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ እንዲሁም የጕበቱን መሸፈኛ ከኵላሊቶቹ ጋራ ዐብሮ አውጥቶ ያቅርብ።

11 ካህኑም ይህን ሁሉ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል።

12 “ ‘መሥዋዕቱ ፍየል ከሆነ፣ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ፤

13 በራሱም ላይ እጁን ይጫንበት፤ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።

14 ከሚያቀርበውም መሥዋዕት ላይ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያቅርብ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ ከሆድ ዕቃው ጋራ የተያያዘውን ሥብ ሁሉ፣

15 ሁለቱን ኵላሊቶች፣ በኵላሊቶቹ ላይና በጐድኑ አጠገብ ያለውን ሥብ፣ እንዲሁም የጕበቱን መሸፈኛ ከኵላሊቶቹ ጋራ ዐብሮ አውጥቶ ያቅርብ።

16 ካህኑም ይህን ሁሉ በእሳት የሚቀርብና ሽታውም ደስ የሚያሰኝ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ሥብ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።

17 “ ‘በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ፣ ሥብ ወይም ደም ከቶ አትብሉ፤ ይህ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የተሰጠ የዘላለም ሥርዐት ነው።’ ”

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告