Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ኢዮብ 35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኤሊሁ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤

2 “ ‘በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ ነኝ’ ማለትህ፣ ትክክል ይመስልሃልን?

3 ደግሞ ‘ያገኘሁት ጥቅም ምንድን ነው? ኀጢአት ባለመሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል።

4 “ለአንተና ዐብረውህ ላሉት ባልንጀሮችህ፣ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ።

5 ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤ ከአንተ በላይ ከፍ ብለው ያሉትንም ደመናት ተመልከት።

6 ኀጢአትህስ ቢበዛ እርሱን ምን ትጐዳዋለህ? ኀጢአትህስ ቢበዛ ምን ያደርገዋል?

7 ጻድቅ ብትሆንም ለርሱ ምን ትሰጠዋለህ? ከእጅህስ ምን ይቀበላል?

8 ክፋትህ የሚጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጆች ብቻ ነው።

9 “ሰው ከጭቈና ብዛት የተነሣ ይጮኻል፤ ከኀያሉም ክንድ ሥር ለመውጣት ለርዳታ ይጣራል።

10 ነገር ግን እንዲህ የሚል የለም፤ ‘ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? በሌሊት መዝሙርን የሚሰጥ፣

11 ከምድር እንስሳት ይልቅ የሚያስተምረን፣ ከሰማይ ወፎችም ይልቅ ጠቢባን የሚያደርገን፣ እርሱ የት አለ?’

12 ከዐመፀኞች ትዕቢት የተነሣ፣ ሰዎች ሲጮኹ አይመልስላቸውም፤

13 በርግጥ እግዚአብሔር ከንቱ ጩኸታቸውን አይሰማም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ አያዳምጣቸውም።

14 ጕዳይህን ፊቱ አቅርበህ፣ ብዙ ጠብቀኸው፣ ግን እንዳላየኸው ስትናገር፣ ታዲያ፣ አንተን እንዴት ይስማህ!

15 ደግሞም፣ ቍጣው ቅጣት እንደማያስከትል፣ ኀጢአትንም ከቍጥር እንደማያስገባ ተናግረሃል።

16 ስለዚህ ኢዮብ አፉን በከንቱ ይከፍታል፤ ዕውቀት አልባ ቃላትም ያበዛል።”

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告