Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ኢዮብ 25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


በልዳዶስ

1 ሹሐዊውም በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2 “ገዥነትና ግርማ የእግዚአብሔር ናቸው፤ በሰማይም ከፍታ ሥርዐትን ያደርጋል።

3 ሰራዊቱ ሊቈጠር ይችላልን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?

4 ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፣ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ይችላልን?

5 በፊቱ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፣ ከዋክብትም ንጹሓን ካልሆኑ፣

6 ይልቁን ከብል የሚቈጠር የሰው ልጅ፣ ትል የሆነውማ ሰው ምንኛ ያንስ!”

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告