Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ኤርምያስ 45 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


ለባሮክ የተነገረ መልእክት

1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት፣ ኤርምያስ በቃል የነገረውን ባሮክ በብራና ላይ ከጻፈ በኋላ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የተናገረው ይህ ነው፤

2 “ባሮክ ሆይ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፤

3 አንተ፣ ‘እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ፤ ከልቅሶዬ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም’ ብለሃል።”

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በምድር ሁሉ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልሁትን እነቅላለሁ።

5 ታዲያ፣ ለራስህ ታላቅ ነገር ትሻለህን? በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ጥፋት አመጣለሁና አትፈልገው፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ሁሉ ሕይወትህ እንዲተርፍልህ አደርጋለሁ።’ ”

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告