Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ዘፍጥረት 36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


የዔሳው ዝርያዎች
36፥20-28 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥38-42

1 ኤዶም የተባለው የዔሳው ትውልድ ይህ ነው።

2 ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የኤሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፂብዖን ልጅ ዓና የወለዳት ኦሆሊባማ፣

3 እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችው የእስማኤል ልጅ ቤሴሞት ነበሩ።

4 ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት።

5 እንደዚሁም ኦሆሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።

6 ዔሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።

7 ብዙ ሀብት ስለ ነበራቸው ዐብረው መኖር አልቻሉም፤ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም።

8 ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።

9 በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤

10 የዔሳው ወንዶች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤

11 የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤

12 የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ቲምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።

13 የራጉኤል ወንዶች ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህ ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው።

14 የፂብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላምና ቆሬ።

15 ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣

16 አለቃ ቆሬ፣ አለቃ ጎቶምና አለቃ አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።

17 የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦ አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ።

18 የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦ አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላምና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።

19 እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።

20 በዚያች ምድር ይኖሩ የነበሩ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣

21 ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።

22 የሎጣን ወንዶች ልጆች፦ ሖሪና ሄማን፤ ቲምናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።

23 የሦባል ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ሽፎና አውናም፤

24 የፂብዖን ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ አያ እና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፂብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው።

25 የዓና ልጆች፦ ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ ኦሆሊባማ፤

26 የዲሶን ወንዶች ልጆች፦ ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን እና ክራን፤

27 የኤጽር ወንዶች ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋን እና ዓቃን።

28 የዲሳን ወንዶች ልጆች፦ ዑፅ እና አራን።

29 የሖሪውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣

30 ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን። እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።


የኤዶም ነገሥታት
36፥31-43 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥43-54

31 በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦

32 የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ላይ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።

33 ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ።

34 ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።

35 ሑሳም ሲሞት፣ በሞዓብ ምድር ምድያማውያንን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ።

36 ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።

37 ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኡል በምትኩ ነገሠ።

38 ሳኡል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።

39 የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማዪቱም ስም ፋዑ ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።

40 ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣

41 ኦሆሊባማ፣ ኤላ፣ ፒኖን፣

42 ቄናዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣

43 መግዲኤል እና ዒራም። እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው የኤዶም ዘሮች የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው፣ የኤዶማውያን አባት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告