ዕዝራ 2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምወደ አገራቸው የተመለሱ ምርኮኞች ዝርዝር 2፥1-70 ተጓ ምብ – ነህ 7፥6-73 1 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው መካከል ከምርኮ ተመልሰው ወደ የራሳቸው ከተሞች፣ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ የመጡት የአገሩ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ 2 የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከሠራያ፣ ከረዕላያ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከመሴፋር፣ ከበጉዋይ፣ ከሬሁም፣ ከበዓና ጋራ ነበር። የተመለሱት የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ 3 የፋሮስ ዘሮች 2,172 4 የሰፋጥያስ ዘሮች 372 5 የኤራ ዘሮች 775 6 የኢያሱና የኢዮአብ ዘር የሆኑት የፈሐት ሞዓብ ዘሮች 2,812 7 የኤላም ዘሮች 1,254 8 የዛቱዕ ዘሮች 945 9 የዘካይ ዘሮች 760 10 የባኒ ዘሮች 642 11 የቤባይ ዘሮች 623 12 የዓዝጋድ ዘሮች 1,222 13 የአዶኒቃም ዘሮች 666 14 የበጉዋይ ዘሮች 2,056 15 የዓዲን ዘሮች 454 16 በሕዝቅያስ የትውልድ ሐረግ የአጤር ዘሮች 98 17 የቤሳይ ዘሮች 323 18 የዮራ ዘሮች 112 19 የሐሱም ዘሮች 223 20 የጋቤር ዘሮች 95 21 የቤተ ልሔም ሰዎች 123 22 የነጦፋ ሰዎች 56 23 የዓናቶት ሰዎች 128 24 የዓዝሞት ዘሮች 42 25 የቂርያትይዓይሪም፣ የከፊራና የብኤሮት ሰዎች 743 26 የራማና የጌባዕ ዘሮች 621 27 የማክማስ ሰዎች 122 28 የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223 29 የናባው ዘሮች 52 30 የመጌብስ ዘሮች 156 31 የሌላው ኤላም ዘሮች 1,254 32 የካሪም ዘሮች 320 33 የሎድ፣ የሐዲድና የኦኖ 725 34 የኢያሪኮ ሰዎች 345 35 የሴናዓ ዘሮች 3,630 36 ካህናቱ፦ ከኢያሱ ቤተ ሰብ የዮዳኤ ዘሮች 973 37 የኢሜር ዘሮች 1,052 38 የፋስኮር ዘሮች 1,247 39 የካሪም ዘሮች 1,017 40 ሌዋውያኑ፦ በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች 74 41 መዘምራኑ፦ የአሳፍ ዘሮች 128 42 የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎቹ፦ የሰሎም፣ የአጤር፣ የጤልሞን፣ የዓቁብ፣ የሐጢጣና የሶባይ ዘሮች 139 43 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ የሲሐ፣ የሐሡፋ የጠብዖት ዘሮች፤ 44 የኬራስ፣ የሲዓ፣ የፋዶን ዘሮች፤ 45 የልባና፣ የአጋባ፣ የዓቁብ ዘሮች፤ 46 የአጋብ፣ የሰምላይ፣ የሐናን ዘሮች፤ 47 የጌዴል፣ የጋሐር፣ የራያ፤ 48 የረአሶን፣ የኔቆዳ፣ የጋሴም ዘሮች፤ 49 የዖዛ፣ የፋሴሐ፣ የቤሳይ፤ 50 የአስና፣ የምዑኒም፣ የንፉሰሲም ዘሮች፤ 51 የበቅቡቅ፣ የሐቁፋ፣ የሐርሑር ዘሮች፤ 52 የበስሎት፣ የምሒዳ፣ የሐርሳ ዘሮች፤ 53 የበርቆስ፣ የሲሣራ፣ የቴማ ዘሮች፤ 54 የንስያና የሐጢፋ ዘሮች፤ 55 የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች፦ የሶጣይ፣ የሶፌሬት፣ የፍሩዳ ዘሮች፤ 56 የየዕላ፣ የደርቆን፣ የጌዴል ዘሮች፤ 57 የሰፋጥያስ፣ የሐጢል፣ የፈክራት ሐፂቦይምና፣ የአሚ ዘሮች፤ 58 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች 392 59 ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ደግሞ ከቴልሜላ፣ ከቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የመጡ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ዘሮቻቸው ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፦ 60 የዳላያ፣ የጦብያና የኔቆዳ ዘሮች 652 61 ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል። 62 እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ። 63 አገረ ገዥውም ኡሪምና ቱሚም የሚይዝ ካህን እስኪነሣ ድረስ እጅግ ከተቀደሰው ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው። 64 የማኅበሩ ቍጥር በሙሉ 42,360 ነበር፤ 65 ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው። 66 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች፣ 67 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው። 68 በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ። 69 እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 5,000 ምናን ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። 70 ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.