አስቴር 10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምየመርዶክዮስ ታላቅነት 1 ንጉሥ ጠረክሲስ እስከ ባሕር ዳርቻ በሚዘልቀው ግዛቱ ሁሉ ላይ ግብር ጣለ። 2 የኀይሉና የብርታቱ ሥራ ሁሉ እንዲሁም ንጉሡ መርዶክዮስን ለዚህ የላቀ ማዕርግ እንዴት እንዳደረሰው የሚናገረው በሜዶንና በፋርስ የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? 3 አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ፣ ከአይሁድ መካከልም ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሰው ነበር፤ ለወገኖቹ መልካም በማድረጉና ለአይሁድም ሁሉ ደኅንነት የቆመ በመሆኑ፣ በብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቹ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነበር። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.