Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

1 ጢሞቴዎስ 2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


ስለ አምልኮ የተሰጠ መመሪያ

1 እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣

2 ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይኸውም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው።

3 ይህ በእግዚአብሔር በአዳኛችን ፊት ደስ የሚያሰኝ ነው፤

4 እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል።

5 አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ መካከለኛ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤

6 ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል።

7 እኔም ለዚህ ነገር የምሥራች አብሣሪና ሐዋርያ እንዲሁም ለአሕዛብ የእውነተኛ እምነት አስተማሪ ሆኜ ተሾምሁ፤ እውነቱን እናገራለሁ፤ አልዋሽም።

8 እንግዲህ ወንዶች በሁሉም ቦታ ያለ ቍጣና ያለ ክርክር የተቀደሱ እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ።

9 እንዲሁም ሴቶች በጨዋነትና ራስን በመግዛት ተገቢ የሆነ ልብስ ይልበሱ እንጂ በሹሩባ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋቸው ውድ በሆኑ ልብሶች አይሽቀርቀሩ፤

10 ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ በመልካም ተግባር ይዋቡ።

11 ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር።

12 ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፤

13 ምክንያቱም አዳም ቀድሞ ተፈጥሯል፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች።

14 ደግሞም የተታለለው አዳም አይደለም፤ የተታለለችውና ኀጢአተኛ የሆነችው ሴቷ ናት።

15 ይሁን እንጂ ሴት በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም ራሷን እየገዛች ብትጸና ልጅ በመውለድ ትድናለች።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告