Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

1 ዜና መዋዕል 8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


የብንያማዊው የሳኦል ትውልድ ሐረግ
8፥28-38 ተጓ ምብ – 1ዜና 9፥34-44

1 ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣ ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣

2 አራተኛ ልጁን ኖሐን፣ ዐምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ።

3 የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ አዳር፣ ጌራ፣ አቢሁድ፣

4 አቢሱ፣ ናዕማን፣ አሖዋ፣

5 ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።

6 በጌባዕ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤

7 ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።

8 ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።

9 ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ ዲብያን፣ ማሴን፣ ማልካምን፣

10 ይዑጽን፣ ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤ እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።

11 ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት።

12 የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤ ዔቤር፣ ሚሻም እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞችን ከነመንደሮቻቸው የቈረቈረ ሻሜድ፣

13 በኤሎን ይኖሩ ለነበሩ ቤተ ሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።

14 አሒዮ፣ ሻሻቅ፣ ይሬምት፣

15 ዝባድያ፣ ዓራድ፣ ዔድር፣

16 ሚካኤል፣ ይሽጳና ዮሐ የበሪዓ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

17 ዝባድያ፣ ሜሱላም፣ ሕዝቂ፣ ሔቤር፣

18 ይሽምራይ፣ ይዝሊያና ዮባብ የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።

19 ያቂም፣ ዝክሪ፣ ዘብዲ፣

20 ኤሊዔናይ፣ ጺልታይ፣ ኤሊኤል፣

21 ዓዳያ፣ ብራያና ሺምራት የሰሜኢ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

22 ይሽጳን፣ ዔቤር፣ ኤሊኤል፣

23 ዓብዶን፣ ዝክሪ፣ ሐናን፣

24 ሐናንያ፣ ኤላም፣ ዓንቶትያ

25 ይፍዴያና ፋኑኤል የሻሻቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ።

26 ሽምሽራይ፣ ሽሃሪያ፣ ጎቶልያ፣

27 ያሬሽያ፣ ኤልያስና፣ ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።

28 እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።

29 የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ። የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።

30 የበኵር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፤ የእርሱም ተከታዮች ጹር፣ ቂስ፣ ባኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣

31 ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩርና

32 የሳምአን አባት ሚቅሎት ነበሩ። እነርሱም ደግሞ ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋራ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።

33 ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ።

34 የዮናታን ወንድ ልጅ መሪበኣል ነው፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።

35 የሚካ ወንዶች ልጆች፤ ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።

36 አካዝ ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዚምሪን ወለደ፤ ዚምሪን ሞጻን ወለደ።

37 ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ረፋያን ወለደ፤ ረፋያ ኤልዓሣን ወለደ፤ ኤልዓሣም ኤሴልን ወለደ።

38 ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦ ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሸዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ይባላል፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ናቸው።

39 የወንድሙ የኤሴቅ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛ ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛ ልጁ ኤሊፋላት።

40 የኡላም ልጆች በቀስት መንደፍ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ እነርሱም በአጠቃላይ ቍጥራቸው አንድ መቶ ኀምሳ ወንዶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯቸው። እነዚህ ሁሉ የብንያም ትውልዶች ነበሩ።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告