1 ዜና መዋዕል 7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምይሳኮር 1 የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ ቶላ፣ ፉዋ፣ ያሱብ፣ ሺምሮን፤ በአጠቃላይ አራት ናቸው። 2 የቶላ ወንዶች ልጆች፤ ኦዚ፣ ረፋያ፣ ይሪኤል፣ የሕማይ፣ ይብሣም፣ ሽሙኤል፤ እነዚህ የየቤተ ሰባቸው አለቆች ናቸው፤ በዳዊት ዘመነ መንግሥት ከቶላ ዘሮች፣ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩት የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺሕ ስድስት መቶ ነበረ። 3 የኦዚ ወንድ ልጅ፤ ይዝረሕያ። የይዝረሕያ ወንዶች ልጆች፤ ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤል፣ ይሺያ፤ ዐምስቱም አለቆች ነበሩ። 4 ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሯቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ሰዎች ነበሯቸው። 5 ከይሳኮር ጐሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተ ሰቦቹ ትውልድ ቍጥር በአጠቃላይ ሰማንያ ሰባት ሺሕ ነበሩ። ብንያም 6 ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል። 7 የቤላ ወንዶች ልጆች፤ ኤሴቦን፣ ኦዚ፣ ዑዝኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ዒሪ፤ በአጠቃላይ ዐምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤ በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው ሃያ ሁለት ሺሕ ሠላሳ አራት ተዋጊ ሰዎች ተመዝግበዋል። 8 የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ ዝሚራ፣ ኢዮአስ፣ አልዓዛር፣ ኤልዮዔናይ፣ ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣ አብያ፣ ዓናቶት፣ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ። 9 በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺሕ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል። 10 የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን። የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣ ብንያም፣ ኤሁድ፣ ክንዓና፣ ዜታን፣ ተርሴስ፣ አኪሳአር፤ 11 እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ ዐሥራ ሰባት ሺሕ ተዋጊዎች ነበሯቸው። 12 ሳፊምና ሑፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ፣ ሑሺም ደግሞ የአሔር ዘር ነው። ንፍታሌም 13 የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ ያሕጽሔል፣ ጉኒ፣ ዬጽር፣ ሺሌም፤ እነዚህ የባላ ዘሮች ናቸው። ምናሴ 14 የምናሴ ዘሮች፤ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥሪኤል ነው። እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርን የወለደች ናት፤ 15 ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ። እኅቱም መዓካ ትባል ነበር። ሌላው ዘሩ ሰለጰዓድ ሲሆን፣ እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት። 16 የማኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ። 17 የኡላም ወንድ ልጅ፤ ባዳን፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው። 18 እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣ አቢዔዝርንና ማሕላን ወለደች። 19 የሸሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤ አሒያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሒ፣ አኒዓም። ኤፍሬም 20 የኤፍሬም ዘሮች፤ ሱቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣ ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣ ልጁ ታሐት፣ 21 ልጁ ዛባድ፣ ልጁ ሹቱላ። ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጋት ሰዎች ተገደሉ። 22 አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት። 23 ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው። 24 ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤትሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት። 25 ልጁ ፋፌ፣ ልጁ ሬሴፍ፣ ልጁ ቴላ፣ ልጁ ታሐን፣ 26 ልጁ ለአዳን፣ ልጁ ዓሚሁድ፣ ልጁ ኤሊሳማ፣ 27 ልጁ ነዌ፣ ልጁ ኢያሱ። 28 ምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞች፣ በስተምሥራቅ ነዓራን፣ በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን፣ እንዲሁም ሴኬምንና መንደሮቿን፣ ከዚያም ዐልፎ ጋያንና መንደሮቿን በሙሉ ያጠቃልል ነበር። 29 በምናሴም ወሰን ላይ ቤትሳን፣ ታዕናክ፣ መጊዶና ዶር ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር። አሴር 30 የአሴር ወንዶች ልጆች፤ ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊ፣ በሪዓ፤ እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር። 31 የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤ ሔቤርና የቢርዛዊት አባት መልኪኤል። 32 ሔቤርም ያፍሌጥን፣ ሳሜርን፣ ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ። 33 የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤ ፋሴክ፣ ቢምሃል፣ ዓሲት፤ የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ። 34 የሳሜር ወንዶች ልጆች፤ አኪ፣ ሮኦጋ፣ ይሑባ፣ አራም። 35 የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤ ጾፋ፣ ዪምና፣ ሰሌስ፣ ዓማል። 36 የጾፋ ወንዶች ልጆች፤ ሱዋ፣ ሐርኔፍር፣ ሦጋል፣ ቤሪ፣ ዪምራ፣ 37 ቤጴር፣ ሆድ፣ ሳማ፣ ሰሊሳ፣ ይትራን፣ ብኤራ። 38 የዬቴር ወንዶች ልጆች፤ ዮሮኒ፣ ፊስጳ፣ አራ። 39 የዑላ ወንዶች ልጆች፤ ኤራ፣ ሐኒኤል፣ ሪጽያ። 40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ ምርጥ ሰዎች፣ ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ። በትውልድ መዝገባቸው እንደ ተጻፈው ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቍጥር ሃያ ስድስት ሺሕ ነበር። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.