1 ዜና መዋዕል 6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምሌዊ 1 የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌርሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ። 2 የቀዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል። 3 የእንበረም ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ፣ ማርያም። የአሮን ወንዶች ልጆች፤ ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር። 4 አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ 5 አቢሱ ቡቂን ወለደ፤ ቡቂ ኦዚን ወለደ፤ 6 ኦዚ ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያ መራዮትን ወለደ፤ 7 መራዮት አማርያን ወለደ፤ አማርያ አኪጦብን ወለደ፤ 8 አኪማአስ ሳዶቅን ወለደ፤ 9 ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤ አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤ ዓዛርያስ ዮሐናንን ወለደ፤ 10 ዮሐናን ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለገለ ነበር፤ 11 ዓዛርያስ አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 12 አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤ 13 ሰሎም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስ ዓዛርያስን ወለደ፤ 14 ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤ ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ። 15 እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም ዐብሮ ተማርኮ ሄደ። 16 የሌዊ ልጆች፤ ጌርሶን፣ ቀዓት እና ሜራሪ። 17 የጌርሶን ወንዶች ልጆች፤ ሎቤኒ፣ ሰሜኢ። 18 የቀዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል። 19 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ሙሲ። በየአባቶቻቸው ቤተ ሰብ የተቈጠሩት የሌዊ ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤ 20 ከጌርሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፣ ልጁ ኢኤት፣ ልጁ ዛማት፣ 21 ልጁ ዮአክ፣ ልጁ አዶ፣ ልጁ ዛራ፣ ልጁ ያትራይ። 22 የቀዓት ዘሮች፤ ልጁ አሚናዳብ፣ ልጁ ቆሬ፣ ልጁ አሴር፣ 23 ልጁ ሕልቃና፣ ልጁ አብያሳፍ፣ ልጁ አሴር፣ 24 ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኡርኤል፣ ልጁ ዖዝያ፣ ልጁ ሳውል። 25 የሕልቃና ዘሮች፤ አማሢ፣ አኪሞት። 26 ልጁ ሕልቃና፣ ልጁ ሱፊ፣ ልጁ ናሐት፣ 27 ልጁ ኤልያብ፣ ልጁ ይሮሐም፣ ልጁ ሕልቃና፣ ልጁ ሳሙኤል። 28 የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ልጁ አብያ። 29 የሜራሪ ዘሮች፤ ሞሖሊ፣ ልጁ ሎቤኒ፣ ልጁ ሰሜኢ፣ ልጁ ዖዛ፣ 30 ልጁ ሳምዓ፣ ልጁ ሐግያ፣ ልጁ ዓሣያ። የቤተ መቅደሱ መዘምራን 6፥54-80 ተጓ ምብ – ኢያ 21፥4-39 31 ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ 32 እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው፣ ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው። 33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋራ ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓታውያን ልጆች፤ ዘማሪው ኤማን፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣ 34 የሕልቃና ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ፣ የኤሊኤል ልጅ፣ የቶዋ ልጅ፣ 35 የጹፍ ልጅ፣ የሕልቃና ልጅ፣ የመሐት ልጅ፣ የአማሢ ልጅ፣ 36 የሕልቃና ልጅ፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የዓዛርያስ ልጅ፣ የሶፎንያስ ልጅ፣ 37 የታሐት ልጅ፣ የአሴር ልጅ፣ የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ፣ 38 የይስዓር ልጅ፣ የቀዓት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የእስራኤል ልጅ። 39 እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተ ቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የበራክያ ልጅ፣ የሳምዓ ልጅ፣ 40 የሚካኤል ልጅ፣ የበዓሤያ ልጅ፣ የመልክያ ልጅ፣ 41 የኤትኒ ልጅ፣ የዛራ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣ 42 የኤታን ልጅ፣ የዛማት ልጅ፣ የሰሜኢ ልጅ፣ 43 የኢኤት ልጅ፣ የጌርሶን ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፤ 44 በስተ ግራቸው በኩል ዐብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጆች፤ የቂሳ ልጅ ኤታን፣ የአብዲ ልጅ፣ የማሎክ ልጅ፣ 45 የሐሸብያ ልጅ፣ የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣ 46 የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣ የሴሜር ልጅ፣ 47 የሞሖሊ ልጅ፣ የሙሲ ልጅ የሜራሪ ልጅ፣ የሌዊ ልጅ። 48 ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔርን ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር። 49 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ ስለ እስራኤል ማስተስረያ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሚከናወነውን ተግባር ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መሥዋዕት የሚያቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ። 50 የአሮን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ ልጁ አልዓዛር፣ ልጁ ፊንሐስ፣ ልጁ አቢሱ 51 ልጁ ቡቂ፣ ልጁ ኦዚ፣ ልጁ ዘራእያ፣ 52 ልጁ መራዮት፣ ልጁ አማርያ፣ ልጁ አኪጦብ፣ 53 ልጁ ሳዶቅ፣ ልጁ አኪማአስ። 54 መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ የመጀመሪያው ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ ከቀዓት ጐሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያዎች እነዚህ ነበሩ። 55 ለእነርሱም በይሁዳ ምድር የምትገኘው ኬብሮንና በዙሪያዋ ያለው የግጦሽ ቦታ ተሰጠ፤ 56 በኬብሮን ዙሪያ የሚገኙት የዕርሻ ቦታዎችና ከተሞች ግን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ተሰጡ። 57 ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ ልብናን፣ የቲርን፣ ኤሽትሞዓን፣ 58 ሖሎንን፣ ዳቤርን፣ 59 ዓሻንን፣ ዮታን፣ ቤትሳሚስን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ። 60 ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣ ጌባዕን፣ ጋሌማን፣ ዓናቶትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ። ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉት እነዚህ ከተሞች በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው። 61 ለቀሩት የቀዓት ዘሮች ደግሞ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ዐሥር ከተሞች ተሰጧቸው። 62 ለጌርሶን ነገድ በየጐሣቸው ከይሳኮር፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌምና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ ድርሻ ላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው። 63 ለሜራሪ ዘሮች በየጐሣቸው ከሮቤል፣ ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተመደቡላቸው። 64 እስራኤላውያንም ከተሞቹን በዚሁ ሁኔታ መድበው ከነመሰማሪያዎቻቸው ለሌዋውያኑ ሰጧቸው። 65 ቀደም ብለው የተጠቀሱትንም ከተሞች ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገድ ላይ ወስደው መደቡላቸው። 66 ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ከተማ ተሰጣቸው። 67 በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን የመማፀኛ ከተሞች ሴኬምን፣ ጌዝርን፣ 68 ዮቅምዓምን፣ ቤትሖሮን፣ 69 ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው። 70 እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ሰጧቸው። 71 ጌርሶናውያን ከዚህ የሚከተሉትን ከተሞች ወሰዱ፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤ 72 ከይሳኮርም ነገድ፣ ቃዴስን፣ ዳብራትን 73 ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤ 74 ከአሴር ነገድ መዓሳልን፣ ዓብዶን፣ 75 ሑቆቅንና፣ ረአብን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤ 76 ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ ሐሞንንና፣ ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ። 77 ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጐሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለውን ወሰዱ፤ ከዛብሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ ቀርታህን፣ ሬሞንና፣ ታቦርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ። 78 ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ ከሚገኘው ከሮቤል ነገድ፣ በምድረ በዳ የሚገኘውን ቦሶርን፣ ያሀጽ፣ 79 ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤ 80 ከጋድ ነገድ በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትን፣ መሃናይምን፣ 81 ሐሴቦንና ኢያዜርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.