Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

1 ዜና መዋዕል 3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


የዳዊት ወንዶች ልጆች
3፥5-8 ተጓ ምብ – 2ሳሙ 5፥14-16 ፤ 1ዜና 14፥4-7

1 ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የበኵር ልጁ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም፣ ሁለተኛው ዳንኤል፣ ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ፣

2 ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣ አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣

3 ዐምስተኛው የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያ፣ ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።

4 እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር። ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤

5 በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።

6 ኢያቤሐር፣ ኤሊሳማ፣ ኤሊፋላት፣

7 ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣

8 ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላሉ፤ በአጠቃላይ ዘጠኝ ነበሩ።

9 ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።


የይሁዳ ነገሥታት

10 የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ የሮብዓም ልጅ አብያ፣ የአብያ ልጅ አሳ፣ የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣

11 የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣

12 የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣ የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣ የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣

13 የኢዮአታም ልጅ አካዝ፣ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ፣

14 የምናሴ ልጅ አሞን፣ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ።

15 የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፤ በኵሩ ዮሐናን፣ ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣ ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣ አራተኛ ልጁ ሰሎም።

16 የኢዮአቄም ዘሮች፤ ልጁ ኢኮንያ፣ ልጁ ሴዴቅያስ።


ከምርኮ በኋላ የነበረው የነገሥታቱ የትውልድ ሐረግ

17 የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፤ ልጁ ሰላትያል፣

18 መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።

19 የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤ ዘሩባቤል፣ ሰሜኢ። የዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፤ ሜሱላም፣ ሐናንያ፤ እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች።

20 ሌሎችም ዐምስት ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ።

21 የሐናንያ ዘሮች፤ ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች።

22 የሴኬንያ ዘሮች፤ ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ ሐጡስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፤ በአጠቃላይ ስድስት ነበሩ።

23 የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤ ኤልዮዔናይ፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዝሪቃም፤ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ።

24 የኤልዮዔናይም ወንዶች ልጆች፤ ሆዳይዋ፣ ኤልያሴብ፣ ፌልያ፣ ዓቁብ፣ ዮሐናን፣ ደላያ፣ ዓናኒ፤ በአጠቃላይ ሰባት ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告