Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

1 ዜና መዋዕል 25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


የቤተ መቅደሱ መዘምራን

1 ዳዊት ከሰራዊቱ አለቆች ጋራ ሆኖ በመሰንቆ፣ በበገናና በጸናጽል ድምፅ እየታጀቡ ትንቢት የሚናገሩትን ከአሳፍ፣ ከኤማንና ከኤዶታም ቤተ ሰብ መካከል መርጦ መደበ፤ ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑትም ሰዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦

2 ከአሳፍ ወንዶች ልጆች፤ ዛኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። የአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሡ አመራር ሥር ነበረ።

3 ከኤዶታም ወንዶች ልጆች፤ ጎዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።

4 ከኤማን ወንዶች ልጆች፤ ቡቅያ፣ መታንያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ሐናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት።

5 እነዚህም ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ የሚያደርጉ የንጉሡ ባለራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ሰጡት። እግዚአብሔርም ለኤማን ዐሥራ አራት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።

6 እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጸናጽል፣ በመሰንቆና በበገና ድምፅ ለሚቀርበው የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሡ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ።

7 እነዚህም ከቤተ ዘመዶቻቸው ጋራ በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑና የተካኑ ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።

8 የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።

9 የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ለዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12 ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ ቍጥራቸውም 12

10 ሦስተኛው ለዛኩር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

11 አራተኛው ለይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

12 ዐምስተኛው ለነታንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

13 ስድስተኛው ለቡቅያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

14 ሰባተኛው ለይሽርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

15 ስምንተኛው ለየሻያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

16 ዘጠነኛው ለመታንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

17 ዐሥረኛው ለሰሜኢ ወጣ፤ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

18 ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

19 ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

20 ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

21 ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

22 ዐሥራ ዐምስተኛው ለኢያሪሙት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

23 ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

24 ዐሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

25 ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

26 ዐሥራ ዘጠነኛው ለመሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

27 ሃያኛው ለኤልያታ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

28 ሃያ አንደኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

29 ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

30 ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12

31 ሃያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቍጥራቸውም 12።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告