Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

1 ዜና መዋዕል 1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም


ከአዳም እስከ አብርሃም ያለው የትውልድ ሐረግ እስከ ኖኀ ልጆች

1 አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣

2 ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣

3 ሔኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖኅ።

4 የኖኅ ወንዶች ልጆች፤ ሴም፣ ካም፣ ያፌት።


ያፌታውያን
1፥5-7 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥2-5

5 የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሜሼኽ፣ ቴራስ።

6 የጎሜር ልጆች፤ አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቶጋርማ።

7 የያዋን ልጆች፤ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮድኢ።


ካማውያን
1፥8-16 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥6-20

8 የካም ወንዶች ልጆች፤ ኵሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን።

9 የኵሽ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰብቃታ። የራዕማ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን።

10 ኵሽ ናምሩድን አባት ነበረ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ።

11 ምጽራይም፦ የሉዳማውያን፣ የዐናሚማውያን፣ የላህቢያውያን፣ የነፍተሂማውያን፣

12 የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው፣ የከስሉሂማውያንና የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።

13 ከነዓንም፦ የበኵር ልጁ የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣

14 የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርጌሳውያን፣

15 የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣

16 የአራዴዎያውያን፣ የሰማሪናውያንና የአማቲያውያን አባት ነበረ።


ሴማውያን
1፥17-23 ተጓ ምብ – ዘፍ 10፥21-31 ፤ 11፥10-27

17 የሴም ልጆች፤ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው። የአራም ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሜሼኽ።

18 አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ።

19 ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፋሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።

20 ዮቅጣንም፦ አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣

21 ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣

22 ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣

23 ኦፊርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው።

24 ሴም፣ አርፋክስድ፣ ሳላ፣

25 ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣

26 ሴሮሕ፣ ናኮር፣ ታራ፣

27 እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለው አብራም።


የአብርሃም ቤተ ሰብ

28 የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ ይሥሐቅ፣ እስማኤል።


የአጋር ዘሮች
1፥29-31 ተጓ ምብ – ዘፍ 25፥12-16

29 ዘሮቻቸው እነዚህ ናቸው፤ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣

30 ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣

31 ኢጡር፣ ናፌስና ቄድማ፤ እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ናቸው።


የኬጡራ ዘሮች
1፥32-33 ተጓ ምብ – ዘፍ 25፥1-4

32 የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው። የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን።

33 የምድያም ልጆች፦ ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።


የሣራ ዘሮች
1፥35-37 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥10-14

34 አብርሃም ይሥሐቅን ወለደ። የይሥሐቅ ወንዶች ልጆች፤ ዔሳው፣ እስራኤል።


የዔሳው ወንዶች ልጆች

35 የዔሳው ወንዶች ልጆች፤ ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ።

36 የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች፤ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም፣ ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ።

37 የራጉኤል ወንዶች ልጆች፤ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ።


በኤዶም የሚኖሩ የሴይር ሰዎች
1፥38-42 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥20-28

38 የሴይር ወንዶች ልጆች፤ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን።

39 የሎጣን ወንዶች ልጆች፦ ሖሪና ሄማም፤ ቲምናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።

40 የሦባል ወንዶች ልጆች፦ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ስፎ እና አውናም። የፂብዖን ወንዶች ልጆች፤ አያ እና ዓና።

41 የዓና ወንድ ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ ሐምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን እና ክራን።

42 የኤጽር ወንዶች ልጆች፤ ቢልሐን፣ ዛዕዋን እና ዓቃን። የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ እና አራን።


የኤዶምያስ ነገሥታት
1፥43-54 ተጓ ምብ – ዘፍ 36፥31-43

43 በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።

44 ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ።

45 ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።

46 ሑሳም ሲሞት፣ በሞዓብ ምድር ምድያማውያንን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ።

47 ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።

48 ሠምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኡል በምትኩ ነገሠ።

49 ሳኡል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።

50 በኣልሐናን ሲሞት ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የእርሱም ከተማ ስም ፋዑ ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የማጥሬድ ልጅ ነበረች።

51 ሃዳድም ሞተ። ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣

52 ኦሆሊባማ፣ ኤላ፣ ፒኖን፣

53 ቄናዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣

54 መግዲኤል እና ዒራም። እነዚህ የኤዶም ዘሮች የነገድ አለቆች ነበሩ።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™

የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.

በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።

The Holy Bible, New Amharic Standard Version™

Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.

Used with permission. All rights reserved worldwide. 

Biblica, Inc.
跟着我们:



广告