Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ማሕልየ መሓልይ 3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሌሊቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ሆኜ፥ ልቤ የምትወደውን ፈለግኹት፤ ፈለግኹት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

2 አሁን ተነሥቼ በከተማው አካባቢ በመንገዶችና በአደባባዮች መካከል ልቤ የምትወደውን እፈልገዋለሁ፤ ፈለግኹት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።

3 እየተዘዋወሩ ከተማውን የሚጠብቁ ሰዎች አገኙኝ፤ እኔም “ልቤ የምትወደውን አይታችኋልን?” ብዬ ጠየቅኋቸው።

4 ከእነርሱም ጥቂት አለፍ እንዳልኩ ልቤ የምትወደውን አገኘሁት፤ እንዳያመልጠኝም አጥብቄ ያዝኩት፤ ወደ እናቴም ቤት ወሰድኩት፤ እኔ ወደተወለድኩበትም ክፍል አስገባሁት።

5 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ! ፍቅር ራሱ ፈቅዶ እስኪነሣ ድረስ ቀስቅሳችሁ እንዳታስነሡት፤ በፈጣን አጋዘንና በምድረ በዳ ዋልያ ስም ዐደራ እላችኋለሁ።


ሦስተኛ መዝሙር ጋብቻ ሠርገኞች፦

6 እንደ ነጋዴ ቅመም መልካም መዓዛ ያላት፥ በዕጣንና በከርቤ መዓዛ እየተወገደ እንደ ጢስ ዐምድ ሆና ያቺ ከበረሓ የምትመጣው ማን ናት?


ሙሽራይቱ፦

7 እነሆ፥ የሰሎሞን ሠረገላ እየመጣች ነው፤ ከእስራኤል ኀያላን መካከል የተመረጡ ሥልሳ የክብር ዘበኞች አጅበዋታል፤

8 ሁሉም በሰይፍ አያያዝ የሠለጠኑና በጦርነትም የተፈተኑ ናቸው፤ በሌሊት ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመመከት እያንዳንዱ ሰይፉን እንደ ታጠቀ ያድራል።

9 ንጉሥ ሰሎሞን በሠረገላው ውስጥ የሚቀመጥበት ዙፋን ከሊባኖስ እንጨት የተሠራ ነው፤

10 የዙፋኑ ምሰሶዎች በብር የተለበጡ ናቸው፤ የራስ ማስደገፊያው በወርቅ ያጌጠ ነው፤ መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ ውስጡ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት በፍቅር አስውበው በጠለፉት ጌጥ የተዋበ ነው።

11 እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት! ንጉሥ ሰሎሞንን ለማየት ኑ፤ እርሱ እጅግ በተደሰተበት በሠርጉ ቀን እናቱ በራሱ ላይ የደፋችለትን ዘውድ ጭኖአል።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
跟着我们:



广告