Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ኢዮብ 35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኤሊሁም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦

2 “ኢዮብ ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነኝ ማለትህ ትክክል ነውን?

3 ‘ኃጢአት ባልሠራ ምን እጠቀማለሁ? ምንስ አተርፋለሁ?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።

4 አሁን እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉ ለባልንጀሮችህ፥ መልስ እሰጣለሁ።

5 “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ከአንተ በላይ ከፍ ብሎ የሚታየውንም ደመና አስተውል።

6 ኃጢአትን ብትሠራ እግዚአብሔርን በምን ትጐዳዋለህ? በደልስ ብታበዛ ምን ታደርገዋለህ?

7 ጻድቅ ብትሆን ለእግዚአብሔር ምን ትሰጠዋለህ? እርሱ ከአንተ ምንም አይፈልግም።

8 ኃጢአት ብትሠራ የምትጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ነው፤ መልካም ሥራ ብትሠራ፥ የምትጠቅመው ሰውን ነው።

9 ሰዎች ጭቈና ሲበዛባቸው ይጮኻሉ፤ ከሚበረታባቸውም እጅ የሚታደጋቸውን ለማግኘት፥ አቤቱታ ያሰማሉ።

10 ነገር ግን ከእነርሱ አንዳቸው እንኳ በሌሊት ጥበቃ የሚያደርገው ፈጣሪ አምላክ ወዴት ነው ብሎ አይጠይቅም።

11 ከእንስሶች አብልጦ ያስተማረን ከወፎችም ይልቅ ጥበበኞች ያደረገን እርሱ ነው።

12 እነርሱ ይጮኻሉ እርሱ ግን ትዕቢተኞችና ክፉዎች ስለ ሆኑ መልስ አይሰጣቸውም።

13 በእርግጥ እግዚአብሔር ከልብ ያልሆነ ጩኸትን አይሰማም፤ ሁሉን የሚችል አምላክም አያተኲርበትም።

14 “ምንም እንኳ እግዚአብሔርን አላየውም ብትል ጉዳይህ በእርሱ ፊት ስለ ሆነ በትዕግሥት ልትጠብቀው ይገባል።

15 እንዲሁም እግዚአብሔር በቊጣው የማይቀጣ፥ የሰውንም ክፋት በቸልታ የሚያልፍ ይመስልሃል?

16 ኢዮብ ሆይ! በከንቱ ንግግር ታበዛለህ፤ ያለ ዕውቀትም ባዶ ቃላትን ትለፈልፋለህ።”

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
跟着我们:



广告