ኢዮብ 25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምቢልዳድ 1 ሹሐዊው ቢልዳድ እንዲህ ሲል መለሰ፤ 2 “ሥልጣንና መፈራት የእግዚአብሔር ነው፤ በላይኛው ግዛቱ በሰማይ ሰላምን ይመሠርታል። 3 የሠራዊቱ ብዛት ሊቈጠር ይቻላልን? የእርሱ ብርሃንስ የማያበራለት ማነው? 4 እንዴት ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ሊገኝ ይችላል? ሰብአዊ ፍጡር ሆኖ እንዴት ንጹሕ ሊሆን ይችላል? 5 እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጨረቃ እንኳ ደማቅ አይደለችም፤ ከዋክብትም በእርሱ ፊት ንጹሖች አይደሉም። 6 በስባሽና ትል የሆነው ሟች ሰውማ ምንኛ የባሰ ነው?” |