Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ኢዮብ 17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “መንፈሴ ደከመ፤ የሕይወቴም ዘመን ሊፈጸም ተቃርቦአል፤ መቃብርም ይጠብቀኛል።

2 የሚሳለቁብኝ ከበቡኝ ዐይኔም የእነርሱን ጥላቻ ይመለከታል።

3 አምላክ ሆይ! ከአንተ በቀር ለእኔ የሚቆምልኝ የለምና አንተው ራስህ ተያዥ ሁነኝ።

4 እነርሱ ተመራምረው ማስተዋል እንዳይችሉ፥ አእምሮአቸውን ዘግተሃል፤ ስለዚህ ድልን እንዲቀዳጁ አታድርግ።

5 ገንዘብ ለማግኘት ብሎ ባልንጀራውን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ ግፉ በልጆቹ ላይ ይደርሳል።

6 እግዚአብሔር የሰዎች መዘባበቻ አደረገኝ፤ ሰዎቹም በፊቱ እንደሚተፉበት ሰው ሆንኩ።

7 ከሐዘን የተነሣ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤ መላ ሰውነቴም እንደ ጥላ ሆኖአል።

8 እውነተኞች በዚህ ነገር ተደናግጠዋል፤ ንጹሖች እግዚአብሔርን በማያምኑ ሰዎች ላይ ተቈጥተዋል።

9 ይሁን እንጂ ጻድቃን ከእውነት መንገድ ፈቀቅ አይሉም፤ ንጹሖችም በብርታት ላይ ብርታትን ይጨምራሉ።

10 ሁላችሁም እንደገና መጥታችሁ በፊቴ ብትከራከሩ ከመካከላችሁ አንድ እንኳ አስተዋይ ሰው አላገኝም።

11 “የዕድሜዬ ዘመን ተፈጽሞአል፤ ዕቅዴና የልቤ ምኞት ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል።

12 እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ቀን ነው ይላሉ፤ ብርሃኑን ደግሞ ሊጨልም ነው ይላሉ።

13 ከእንግዲህ ወዲህ የሚኖረኝ ዕድል ፈንታ ወደ ሙታን ዓለም መውረድ ነው፤ እዚያም በጨለማ አልጋዬን እዘረጋለሁ።

14 መቃብርን ‘አባቴ’ ብዬ እጠራዋለሁ፤ የሚበሉኝንም ትሎች ‘እናቴና እኅቴ’ እላቸዋለሁ።

15 ታዲያ፥ እኔ ምን ተስፋ አለኝ? ተስፋ የሚሆነኝንስ ነገር ማን ያይልኛል?

16 እኔ ወደ ሲኦል ስወርድ ተስፋ አብሮኝ ይወርዳልን? አብረንስ ወደ መቃብር እንወርዳለንን?”

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
跟着我们:



广告