Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -

ዕብራውያን 6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እንግዲህ ስለ ክርስቶስ የተሰጠውን የመጀመሪያ ትምህርት ትተን ፍጹም ወደህ ኦነው ትምህርት እንለፍ፤ ከሞተ ሥራ ንስሓ የመግባትንና በእግዚአብሔር የማመንን መሠረት እንደገና አንመሥርት፤

2 እንዲሁም የጥምቀትን፥ የእጅ መጫንን፥ ከሞት የመነሣትን፥ የዘለዓለም ፍርድን ትምህርት እንደገና አንመሥርት።

3 እግዚአብሔር ቢፈቅድልን ይህን እናደርጋለን።

4 እምነታቸውን የካዱትን ሰዎች ወደ ንስሓ መመለስ እንዴት ይቻላል? እነዚህ ሰዎች ከዚህ በፊት ብርሃን በርቶላቸው ነበር፤ ሰማያዊውንም ስጦታ ቀምሰው ነበር፤ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ተካፋዮች ሆነው ነበር፤

5 የእግዚአብሔርን መልካም ቃልና የሚመጣውን ዓለም ኀይል ቀምሰው ነበር፤

6 ከዚህ ሁሉ በኋላ እምነታቸውን ቢክዱ እነርሱ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና ስለሚሰቅሉትና በይፋ ስለሚያዋርዱት እነርሱን ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም።

7 ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ ተክል ለተከለባትም ሰው ጥቅም የምትሰጥ መሬት ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለች።

8 እሾኽና አሜከላ ብታበቅል ግን ዋጋቢስ ትሆናለች፤ በቅርብ ጊዜም ትረገማለች፤ መጨረሻዋም በእሳት መቃጠል ነው።

9 ተወዳጆች ሆይ! ይህን ብንናገርም እንኳ እናንተ መዳናችሁን በሚያመጣ የተሻለ አቋም ላይ ለመሆናችሁ እርግጠኞች ነን።

10 እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው፤ ስለዚህ ሥራችሁንና በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።

11 እናንተ ሁላችሁም በተስፋ የምትጠባበቁትን ነገር እስክትጨብጡ ድረስ ትጋታችሁን እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን፤

12 የምንመኘውም በእምነትና በትዕግሥት ጸንተው ተስፋ የተሰጣቸውን ነገር የሚወርሱትን ሰዎች እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንድትሆኑ አይደለም።


የእግዚአብሔር ተስፋ አስተማማኝነት

13 እግዚአብሔር ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ የሚምልበት ከእርሱ የበለጠ ሌላ ማንም ስለሌለ እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፤

14 “በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ።”

15 አብርሃም በትዕግሥት ጠብቆ ተስፋ የተደረገለትን ነገር አገኘ።

16 ሰዎች ሲምሉ ከራሳቸው በሚበልጥ ስም ይምላሉ፤ ንግግራቸውንም በመሐላ በማጽናት በመካከላቸው ያለውን ክርክር ሁሉ ያስወግዳሉ።

17 በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ውሳኔው የማይለወጥ መሆኑን ለማስረዳት ፈልጎ ለተስፋው ወራሾች ተስፋውን በመሐላ አጸናላቸው።

18 በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።

19 ይህ ተስፋ ለሕይወታችን እንደማይነቃነቅ አስተማማኝ መልሕቅ ነው፤ በኢየሱስ ያለን ተስፋ መጋረጃውን አልፎ ወደ መቅደስ ይገባል።

20 ወደዚህም መቅደስ ኢየሱስ እንደ መልከጼዴቅ የክህነት ሹመት ለዘለዓለም የካህናት አለቃ ሆኖ ስለ እኛ ቀድሞ ገብቶአል።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
跟着我们:



广告